ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
24

የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት/ቤት በብ/የሚ/የግ/ግክ/ቡድን በ2018 በጀት አመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች ማለትም፡- የደን ዘር፣ የደጋ ፍራፍሬ እና ፖሊቲን ቲዩብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የተለያዩ ግብዓቶች ማለትም፡-
  • ሎት የደን ዘር ጌሾ 150 ኪ/ማ፤ ግራቪሊያ 40 ኪ/ግ እና ወይራ 20 ኪ/ግ ሁኖ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና ከኳራንታይን የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ሎት የተጣበቀ የአኘል ችግኝ በቁጥር 2,550 /ሁለት ሽህ አምስት መቶ ሃምሳ/ ጥራት፡-
  • የችግኝ ቁመት3 ሜትር ቁመት ያለው የተስተካከለና ቀጥ በሎ የወጣ መሆን አለበት፡፡ የከተባ ቦታው የግራፍት ቦታ ከመሬት ከ20-30 ሴ.ሜ፣ ከፍታ ላይ የሆነ የችግኙ ግንድ ውፍረት ከግራፍት ከፍታው 10 ሳ.ሜ ከፍ ብሎ ወይም ከመሬት 25 ሳ.ሜ ከፍታ በላይ 11.ሜ.ሜ ዲያሜትር ያለው፤ ችግኙ በሁሉም አቅጣጫ ስር ያለውና ከበሽታና ከተባይ የፀዳ መሆን አለበት፡፡
  • ከኳራንታይል የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችልና ዝርያውን ሊገልጽ የሚችል ችግኝ፡፡
  • ሎት የደጋ ፍራፍሬ የአፕል መሰረተ ግንድ በቁጥር 11,000 ዝርያው mm106 ሁኖ የችግኙ ቁመት 1.3 ሜትር እና ተስተካክሎ ቀጥ ብሎ የወጣ ችግኙ በሁሉም አቅጣጫ ስር ያለው፣ ከበሽታ እና ተባይ የፀዳ እና የችግኙ ውፍረት ከእርሳስ ቅርጽ ያላነሰ ወይም ያልወፈረ ሆኖ የሚቀርብበት ቦታ ፋሲለደስ ችግኝ ጣቢያ ከኳራንታይን የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ሎት 4. ፕላስቲክ ወይም ፖሊቲሊን ቲዩብ 3 ኩ/ል ዲያሜትሩ ባለ 10 ሴ/ሜ እና ነጭ የሆነ፣ ፕላስቲክ 3 ኩ/ል ዲያሜትሩ 14 ሴ/ሜ ጥቁር የሆነ፡፡
  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ፣ የአሰሪው መ/ቤት እና የተጫራቾች ሙሉ ስም አድራሻ ፊርማ ማህተም በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) የማይመለስ ብር በመክፈል ከቢ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ደ/ስራ/ሂ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት /በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ ሚያዚያ 19/2018 ዓ.ም ዓ.ም እስከ ግንቦት 03/2018 ዓ.ም 10፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን 11፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
  5. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ጽ/ቤት በብ//የሚ/የግ//ግ/ክ/ ቡድን በቢሮ ቁጥር 06 ግንቦት 04/2018 ዓ.ም በ3፡00 ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን 20 በመቶ የመጨመርም የመቀነስም መብቱ የተጠበቀነዉ፡፡
  8. መ/ቤቱ ጨረታውን በሚከፍትበት ቀን ብሄራዊ በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ደን ዘር፣ ፖሊቲዩን ቲዩብ እና አትክልት ዘር የሚቀርበው በግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ሲሆን በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል፡፡
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 06 04 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡

የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here