በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
21

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት የሰራተኛ ደንብ ልብስ በግልት ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ  የሚከተሉን መስፈርቶች መሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደስ ንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋው ላይ 2 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ የሚችሉ ሆኖ አሸናፊው ከተለየና ውል ከተያዘ በኃላ ያልተመረጡ ተጫራቾች ያሰያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለመጫረት የሚፈልጓቸውን ዕቃዎች ናሙና ለማቅረብና በተመረጡ ናሙናዎች ላይ የዋጋ ውድድር ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ብር 300 (ሦስት መቶብር) በመክፈል ባ/ዳር ከተማ ጊዮርጊስ ስካይ ሪዞርት አጠገብ በሚገኘው ኢባትሎ ባ/ዳር ት/ጽ/ቤት ሰነዱን በመግዛት ዝርዝር መረጃውን ማግኝት ይችላሉ፡፡
  5. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15 ተኛው ቀን ቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ስምና ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን ማሰፈርና የድርጅቱን ማህተም በትክክል ያረፈበት ሆኖ በፖስታ በማሸግ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማሰገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ዋጋው ታክስን ጨምሮ በትክክል ተሞልቶ መቅረብ አለበት፡፡
  8. ጨረታው የሚገመገመው በተናጠል በሚቀርብ ዋጋ ይሆናል፡፡
  9. ሎጅስቲክሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሰልክ ቁጥር 058 320 70 44 /058 220 88 91 ደውሎ ወይም ባ/ዳር ከተማ ጊዮርጊስ ስካይ ሪዞርት በሚገኘው ቢሮችን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ

ባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here