ፈጣኑ ሮቦት

0
12

በቻይና ሁለት ኩባንያዎች በሰከንድ 10 ሜትር  መሮጥ የሚችል ሮቦት ማምረታቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል::

የምንጊዜም ፈጣኑ ሯጭ ዩዜን ቦልት በራሱ የተያዘው ክብረወሰን በሮቦቶች ሊሰበር ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል-በተመልካቾች ዘንድ::

የቻይናው “ዩኒትሪ” የተሰኘው ግዙፍ ሮቦት አምራች ኩባኒያ በቅርቡ ለትሪኢት ያቀረበው “ኤች1” የተሰኘ ምርቱ 100 ሜትር ሲፈተለክ 10 ሜትሩን በሰከንድ መሮጥ መቻሉ ተረጋግጧዋል::

ዩዜን ቦልት በ2009 እ.አ.አ 9.58 ሜትርን በሰከንድ የሮጠ ሲሆን አማካዩ 10.44 ሜትርን በሰከንድ መሆኑ ተጠቁሟል::እናም ይሄው የፍጥነት ክብረወሰን በ”ኤች1” ሮቦት መመዝገቡን ድረ ገጹ አስነብቧል::

አሁን ላይ የዩኒትሪ ሮቦት አምራቹ ኩባንያ ምርት የሆኑት በአጭር ርቀት የመፈትለክ አቅማቸው 10.1 ሜትር በሰከንድ ተመዝግቧል::በሰአት ምዝገባ ላይ የተወሰነ ውስንነት መኖሩን ያስነበበው ድረ ገጹ አጠቃላይ አፈጻጸሙ ግን የተሻለ ምዕራፍ ላይ መሆኑን ነው ያመላከተው::በዚህም ከእስከአሁኑ ሁሉ ክብረወሰን የያዘ ሆኗል::

ባለፉት አመታት የቻይና ሮቦት አምራቹ ኩባንያ”ስታር1” ስምንት ማይል በሰአት መሮጡ ነበር የተመዘገበው::ሮቦት አምራቾቹ ኩባንያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመኑ የሚያመርቷቸው ምርቶች እየተራቀቁ መጥተው የዩዜን ቦልትን ፍጥነት የተቃረበ  10 ሜትር በሰከንድ  ያስመዘገበው አዲስ እመርታ መሆኑ ነው በማጠቃለያነት የሰፈረው::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here