የዓየር ንብረትን የሚቀርፀው ድብቁ ኃይል

0
14

በዓየር ሁኔታ መከታተያ ሳተላይቶች የሚቀረጹ በውቅያኖስ ላይ  የሚፈጠሩ ሞገዶች ለውጦች እና ደብቅ እንቅስቃሴዎች በየብስ የዓየር ንብረት ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፉ ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ለንባብ አብቅቶታል::

የባሕር ላይ ሞገዶቹ የዓየር ንብረትን እና የባህር ስነምህዳሮች የካርበን ክምችት ሂደትን ለመረዳት ቁልፍ መሆናቸው ነው የተጠቆመው- በአሜሪካ የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ቡድን:: ተመራማሪዎቹ ሁነቱን ለመረዳት “ጐፍሎው”  ወይም (ጆኦስቴሽነሪ ኦሺን ጎፍሎው” ስልትን ነው የተጠቀሙት፤ ይህም መረዳት የቻሉት  በህዋ ውስጥ የዓየር ንብረቱን ለመከታተል በመጠቁ  ሳተላይቶች የተነሳን ወይም የተቀረፀን ምስል በኮምፒዩተር በጥልቀት ገምግመው ውጤቱን በመቀመር ነው::ተመራማሪዎቹ አዲሱን ስልት ለመተግበር ወደ ህዋ የመጠቁ ሰውሰራሽ ሳተላይቶችን እንጂ ሌላ ተጨማሪ መሣሪያ ማምጠቅ እንደማይጠበቅባቸው ነው ያስረዱት:: የውቅያኖስ ሞገዶች ለአየር ንብረት እና ለህይወት ያላቸውን አስፈላጊነት- ሙቀትን በማንሸራሸር፣ በከባቢ ዓየር እና በጥልቅ ውቅያኖስ መካከል “ካርበን”ን በማስተላለፍ እና የባሕር ውስጥ ስነ ምህዳርን የሚደግፉ ንጥረ ነገሮችን በማሰራጨት ላይ የተመሰረተ መሆኑም ነው የተሰመረበት::

ለተመራማሪዎቹ ቡድን ከውቅያኖስ የላይኛው ወለል  ወደ ታችኛው ጥልቅ ወለል፣ ከጥልቁ ወለል ወደ ላይኛው (ቨርቲካል) ወይም ሽቅብ የውኃ ድብልቅ መቼ እንደሚካሄድ አለማወቃቸው ሰፊ ክፍተት ሆኖ መቆየቱን ድረ ገጹ አስነብቧል::  አሁን ላይ ይህንን ሂደት መረዳት ወሳኝ መሆኑንም ነው ያሰመሩበት- ምክንያታቸው ደግሞ ከጥልቅ ውቅያኖስ ንጥረ ነገሮች ወደ ላይ በማውጣት እና ካርበንን ከላይ ወደ ታችኛው ወለል በማስረግ የባህር ውስጥ ህይወትን ይደግፋልና ነው:: ተመራማሪዎቹ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በወቅያኖስ ላይ የሙቀት ሞገዶች እንዴት በዓየር እንቅስቃሴዎች ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፉ መገንዘባቸውንም ነው በማጠቃለያነት ያሰፈሩት::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here