ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
14

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ለምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚሰጥ በወረዳችን እያጋጠመን ያለዉን የመጋዝን ችግር ለመቅረፍ ቆላድባ ከተማ ላይ ዘመናዊ መጋዝን ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገነባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግንባታ ፈቃድ ከደረጃ 6 እና በላይ መሆን አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ  ሰነዳቸዉ ጋር  አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከሚያዚያ 26/2018ዓ.ም ጀምሮ የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የመጋዝን ግንባታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሻናፊዉ የሚለየዉ በሎት ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 ከሚያዚ 26/2018 ዓ/ም እስከ ግንቦት 16/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ  የባንክ ዋስትና  ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝን በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  10. በጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግንቦት 17/2018 ዓ.ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን ግንቦት 17/2018 ዓ/ም በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለዉ፡፡
  12. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁደ ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  14. ተጫራቾቹ በጨረታዉ ማሸነፉ እና የዉል ስምምነት እንዲፈጽም በተገለጸበት ጊዜ ከአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በህጋዊ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ  ደረሰኝ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን የሞላዉ ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ በታች ከሆነ ዉድቅ እንደሚሆን እንገልጻለን፡፡
  15. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 32 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር  ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም

የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here