በአፈ/ከሳሽ ወ/ሮ ለምለም ፍሬው እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ አደራ ቸኮል መካከል ባለው የጋብቻ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ኮ/ር ዕድሜ አለም፣ በምዕራብ እና በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ቻላቸው መኮነን ተዋስኖ የሚገኘው ቤት በአቶ አደራው ቸኮል ስም የተመዝገበ የፍርድ ባለእዳ የሆነው የሊዝ እዳ ያለበት በመነሻ ዋጋ በብር 3,367,344.08 (ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አራት ብር ከዜሮ ስምንት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ ስለሆነም ከሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

