የአብክመ ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በeTAS በጀት ኤሌክትሮኒክስ፣ Advanced CI/CD Technical Training for IT Experts አገልግሎት ግዥ እና በመደበኛ በጀት የካሜራ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ለማቅረብ የሚችሉና ህጋዊ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች ሁሉ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)፣ Advanced CI/CD Technical Training for IT Experts ብር 40,000. (አርባ ሺህ ብር) እና የካሜራ ግዥ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አብክመ ገቢዎች ቢሮ ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር 313 ኤሌክትሮኒክስ እና Advanced CI/CD Technical Training for IT Experts የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) እንዲሁም የካሜራ ግዥ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቅዳሜ 6:30 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡ ሁኖም አስራ ስድስተኛው (16ኛዉ) ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል፡፡
- ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
አድራሻችን፡- ባሕር ዳር ቀበሌ 16 ሜድሮክ ጀርባ እና የድሮው ዶ/ር ፍሬው የነበረው የአሁኑ ዶ/ር አዲሱ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 058 226 57 65 ወይም 058 226 61 71 በመደወል መረጃ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የአብክመ ገቢዎች ቢሮ

