በአፈ/ከሳሽ አቶ ምህረት አለም እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ ደረጀ የኔት መካከል ባለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መለሰ አዳል፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ደረጀ የኔት እንዲሁም በደቡብ ሙሉአለም ተዋስኖ የሚገኘው መኖሪያ ቤት በአቶ ደረጀ የኔት ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ቤት በመነሻ ዋጋ በብር 3,897,543.08 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አምስት መቶ አርባ ሶስት ብር ከሰማንያ ሶስት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ በመሆኑም ከሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 26/2018 ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እንዲሸጥ ሲል ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንድትቀርቡ፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

