የሊዝ ቦታ ጨረታ ማስታወቂያ

0
21

የሰሜን ወሎ ዞን የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት የሊዝ ጨረታ ኮሜቴ የከተማ ቦታን በሊዝ ሰለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ቁጥር ከሀ እሰከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም  መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም አካል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ ማወቅ እና የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል በመሬት ማስተላለፍ  ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ዘወትር በስራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ የጨረታዉ አይነት የጨረታዉ ዙር የቦታዉ መገኛና ቀበሌ የቦታዉ ስፋት የቦታዉ አገልግሎት ለቦታዉ የተሰጠዉ የጨረታ ኮድ ቁጥር
1. መደበኛ 4ኛ ዙር 01 ቀበሌ ከያፌት መድሀኒት መደብር በስተምዕራብ 208 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 01
2.  ›› ›› 01 ቀበሌ ከያፌት መድሀኒት መደብር በስተምዕራብ 208 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 02
3. ›› ›› 01 ቀበሌ   አባሀቀየ ከመስጅዱ በስተ ደቡብ 148.5 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 03
4. ›› ›› 01 ቀበሌ  ከተመቸ ሆቴል በስተ ምሥራቅ በኩል 352 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 04
5. ›› ›› መርሳ 01 ቀበሌ በርበሪ ገንዳ አካባቢ 702 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 05
6. ›› ›› 03 ቀበሌ ከመርሳ ጤና ጣቢያ በስተምዕራብ 1414.5 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 06
7. ›› ›› 03 ቀበሌ ከመርሳ ጤና ጣቢያ በስከ ምዕራብ 1414.5 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 07
8. ›› ›› 03 ቀበሌ ከመርሳ ጤና ጣቢያ በስከ ምዕራብ 1414.5 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 08
9. ›› ›› 03 ቀበሌ ከመርሳ ጤና ጣቢያ በስከ ምዕራብ 1414.5 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 09
10. ›› ›› 03 ቀበሌ ከመርሳ ጤና ጣቢያ በስከ ምዕራብ 1435 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 10
11. ›› ›› 03 ቀበሌ ከመርሳ ጤና ጣቢያ በስከ ምዕራብ 1435 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 11
12. ›› ›› 03 ቀበሌ ከመርሳ ጤና ጣቢያ በስከ ምዕራብ 1435 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 12
13. ›› ›› 03 ቀበሌ ከመርሳ ጤና ጣቢያ በስከ ምዕራብ 1435 ካ.ሜ ለድርጅት አገ/ት 13

 

  1. ጨረታው ዙር፡- 4ኛ ዙር የ2018 ዓ.ም
  2. የጨረታው ዓይነት፡- መደበኛ
  3. ቦታው ከማንኛውም ክርክር ነፃ ነው
  4. ቦታው ደረጃ 1ኛ
  5. በቦታው የሚፈቀደው አገልግሎት አይነት የህንፃው ከፍተኛ የግንባታ ወለል ግቢ ስፋት ንጽጽር በፕርስንት ሆኖ ቦታው ለሆቴል፤ ለምግብ አዳራሽ ለመኝታ አገልግሎት የሚውል ሲሆን ከፍታውም G+4 ፎቅና ከዚያ በላይ ሆኖ 70 በመቶ የቦታው ስፋት በግንባታ ይሸፈናል፡፡
  6. የጨረታው መነሻ የሊዝ ዋጋ ለአንድ ካሬ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ ነው፡፡
  7. የሚፈለገው አነስተኛ የቅድሚያ ክፍያ መጠን አጠቃላይ የቦታውን ዋጋ 30 በመቶ ይሆናል፡፡
  8. የቀሪ ክፍያ ማጠናቀቂያ መጀመሪያ ክፍያ ከተከፈለበት ከ2 ዓመት የእፎይታ ጊዜ በኋላ ጀምሮ እሰከ ሊዝ ዘመኑ 40 አመት (አርባ) ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ እንደተገለፀለት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ዋጋ 30 በመቶ ያላነሰ ቅድሚያ ክፍያ ወይም በቴክኒካል ፕሮፖዛሉ ላይ የገለፀውን ቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም ውል ይፈፀማል፡፡ በተጠቀሰው ቀን በሚሰጠው ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ 2ተኛ የወጣው አንደኛ የወጣውን ዋጋ በመስጠት መውሰድ ከፈለገ ይሰጠዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የተጫረተበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማብዛት የሚገኘውን ውጤት 10 በመቶ ያላነሰ በኦርጅናል ፖስታ ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በማድረግ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ታሽጎ በጽሁፍ ለይተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የቦታ ዋጋ በፊደልና በአሀዝ መሙላት ይኖርበታል፡፡ በፊደልና በአሀዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፌደል የተፃፈው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
  13. አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይቻልም ገዝቶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  14. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚጀምርበት ጊዜ ከሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም ዓ.ም እስከ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም ዓ.ም በአስር የስራ ቀናት ከቀኑ እስከ 11፡00 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  15. በሰነድ ማሳሰቢያው ሀሳብ ላይ በፊደልና በአሀዝ የተፃፈው ሥርዝ ድልዝና የሚያምታታ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  16. የጨረታው የሰነድ ሽያጭ የሚያልቅበት ግንቦት 10/2018 ዓ.ም ዓ.ም በ9:00 ይሆናል፡፡
  17. ሰነዱን በመሬት ልማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት) በመምጣት በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  18. ቦታውን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በማንኛውም የስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  19. ጨረታው የሚከፈተው ግንቦት 11/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 በመርሳ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  20. መስሪያ ቤቱ በጨረታው ካልተስማማ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
  21. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 033 333 00 68 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የመርሳ ከተማ አስ/ር መሬት ፅ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here