ሴቶች እና ምርጫ 

0
106

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ (2000) አንቀጽ 1325  የስርዓተ-ፆታ አመለካከትን በማዋሃድ እና ለመመስረት ያለመ ስምምነቶች  መደረጉ ለሀገራት የተረጋጋ ሰላም መሠረት ነው ይላል። እ.ኤ.አ በ1995 አራተኛው የዓለም የሴቶች ኮንፈረንስ ላይም ሰላም እና እኩልነት በማይነጣጠል ሁኔታ የተሳሰረ ነው በሚል እምነት የሴቶች እና የወንዶች እኩልነት እና በሁሉም መልኩ ማጠናከር በተለይም የሚወክላቸውን አካል በእኩል ምርጫ ተሳትፎ መምረጥ ሊኖር እንደሚገባ ያሳስባል፡፡

የፕሬዝዳንታዊ ምርጫን በ1778  የጀመረችው አሜሪካ የሴቶችን የመምረጥ መብት በሕግ ያጸደቀችው በ1920፣ ከ142 አመታ በኋላ ነበር። ይህም የአሜሪካ ሴቶች መብታቸውን ለማረጋገጥ ከመቶ አመት በላይ የፈጀ ትግል እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል ።

ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የሴቶችን የመምረጥና የመመረጥ መብት ለመጀመሪያ ጊዜ በተግባር ያስከበረችው ሀገር ኒውዚላንድ ናት፤ በአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1893 ነው። የመጨረሻዋ ደግሞ ሳውዲ አረብያ፣ በ2015/16 እ.አ.አ ነው። በ1949ዓ.ም በኢትዮጵያ በተካሄደው የመጀመሪያው ምርጫ ከ ሦስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለመምረጥ ተመዝግበው ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ የሆኑት መርጠዋል። በዚህ ምርጫ ታድያ የሴቶች ተሳትፎም ጀምሮ ነበር።  ይህም የሚያሳየው ሀገራችንን ጨምሮ በሁሉም የዓለም ክፍል ሴቶች ከወንዶች እኩል የመምረጥ እና የመመረጥ መብት እንዳላቸው በህገ መንግስት ጭምር ቢያስቀምጡም በሁለቱም በኩል ያለው ተሳትፎ ሲታይ ግን የብዛታቸውን ያህል በቂ አለመሆኑን  ዩኤን ኦርግ ድረ ገፅ ጥናት በማድረግ ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሴቶቹ መብት እንዳላቸው ከተቀመጠ ያለባቸው መሰናክሎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ ባደረገው ዳሰሳ የተገኘው ውጤት  በማህበረሰቡ ያለው የሥርዓተ-ፆታ አመለካከቶች ችግር ፣ በሴቶቹ በኩል ያለው  የስነ-ልቦና እና ባህላዊ መሰናክሎች፣ ትምህርት ( ዕውቀት አለመኖር)፣ ድህነት (የኢኮኖሚ ጥገኝነት)፣  የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳታፊነት ችግር፣ ብሄረሰቦች ወይም ጎሳዎች ጠንካራ መሪን አብዛኛውን ጊዜ ለወንድ መሥጠት  ችግሮችን በዋና ችግርነት ያነሳሉ።

ዩኤን ዲፒ ባደረገው ሌላ ጥናት ደግሞ በምርጫ ሂደቶች ውስጥ መሳተፍ ድምጽን ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሮችን ያካትታል ፖለቲካዊ ተሳትፎ የመናገር ፣ የመሰብሰብ እና የመሰብሰብ ነፃነትን ያስገኛል። የፖለቲካ ሂደቱ በተግባር ግን ብዙውን ጊዜ ሴቶች ይህንን መብት ለመጠቀም በጣም ከባድ ነው በቅርብ አሥርተ ዓመታት ውስጥ ግን ሴቶችን የማካተት እና የማብቃት ፍላጎቶች በሁሉም መንግስታት  እያደጉ መጥተዋል ይላል። የዴሞክራሲያዊ ፖሊሲዎች ቁልፍ እሴቶች ውስጥ የሴቶች ማህበራዊ ክፍተቶች በመሙላት ድምጽ እንዲኖራቸው የፖሊሲ አወጣጥ ሂደት፣ ላይ እንዲሁም ከፖለቲካ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ቡድኖች ብሄረሰብ፣ ክልልሎች፣ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ ወይም ትምህርት ጋር ያለውን ችግር በደንብ በመረዳት ሴቶችን ማስገንዘብ ይጠይቃል።

በፖለቲካ ሕይወት ውስጥ ወንዶችና ሴቶች የዳሰሳ ጥናት (Women Voter Servey) በበኩሉ ከ2005 እስከ 2006 እ.አ.አ በተደረገ ጥናት በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ጠይቆ በአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ስዊድን፣ አርጀንቲና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ እስራኤል፣ ታንዛኒያ፣ ቬትናም እና ግብፅ በወንዶች መካከል ያለው ልዩነት እና የሴቶች ተሳትፎ መጠን ወሳኝ የሚባል ቁጥር አልነበረም፡፡ የማሌዢያ ሴቶች ከወንዶች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ የመምረጥ እና የመመረጥ መብት ነበራቸው፤ እ.ኤ.አ ከ1957 እስከ 1959 ከወንዶች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ፓርላማ እየተመረጡ ነበር።

ሆኖም በ2005 ሴቶች እ.ኤ.አ. በሚኒስትር ደረጃ ያለው መንግሥት ከጠቅላላው ቁጥር 9 ነጥብ 1 በመቶውን ብቻ ይዟል። ማለትም በታችኛው ምክር ቤት በመቶ  25 ነጥብ 7 በመቶ በላይኛው ምክር ቤት ወይም ሴኔት ውስጥ በስቴቱ ውስጥ ያለው  ደረጃ 6 በመቶ ብቻ የሴቶች አባላት አሉት ይላል፡፡ በብዙ ሀገሮች የሴቶች መብት በሕግ የተደነገገ ሲሆን መደበኛ የሚባል ችግር እንደሌለ ይሄኛው ጥናት ጠቁሞ፤ በምርጫ ሂደቶች ግን  የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ  መሰናክሎች አሉ ይላል፡፡ የሴቶችን ጥቃቀን ችግሮች ለመፍታት  እና ሥር ነቀል ፖለቲካ ማሻሻያ ለማድረግ በመረባረብ “ትናንሽ ጥያቄዎች” ለመመለስ የሚደረጉ ሙከራዎች ውጤታማ አለመሆናቸው ሴቶቹ ለፓለቲካ ትኩረት እንዳይሠጡ ያደርጋል።

አብዛኞቹ ሴቶች ፓርቲዎች ስለሚያስቡት ነገር ደንታ የሌላቸው፣ ለሕዝብ ጥቅም በቂ ምላሽ የማይሰጡ መሆናቸውን የሚያምኑ መሆኑ፣  እምነት ጥለው ሊሳተፉ እንዳይችሉ አድርጎታል፡፡ በሌላ በኩል ሴቷ ያለባት ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ጫና ፣ ፖለቲካ እና በፍላጎት እንዳትገልፅ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡  አንዲት ሴት ከቤተሰቧ ፍላጎት ውጪ ለራሷ ቦታ እና ድምፅ መደራደር የምትችል እንደሆነ ማሳየት እንደምትችል በሰፊው ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ ያነሳው ጥናቱ ፤ ይህ ከተደረገ በፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆን እና ይህ ፓርቲ ለኔ ይገባኛል፣ ይሆነኛል የሚል ፍላጎት እና ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ ማድረግ ማስቻል ይገባል፡፡ ይህ  ተግባር ለነሱ የሚገባ መሆኑን እና ሴቶች እኩል መሆናቸውን አጉልቶ ሊያሳያቸው ይችላል እና ይህን ማድረግ ወደ ፊት ሊሠራው የሚገባው ስለመሆኑ ጥናቱ አስፍራል፡፡

ማናት

ወ/ሮ ብርሃኔ አስፋው

በ1931 ዓ.ም.  በጎንደር የተወለዱት ወ/ሮ ብርሃኔ አስፋው ፡፡ ወ/ሮ ብርሃኔ ከራስ ዳሸን ተራራ ስር አድገው እስከ ሦስተኛ ክፍል ከተማሩ በኋላ ቤተሰባቸው ወደ ደሴ በመዘዋወሩ አብዛኛውን የትምህርት ሕይወታቸውን ደሴ ነው ያሳለፉት።

በወ/ሮ ስኂን እና እቴጌ መነን ትምህርት ቤቶች ተምረው በቀድሞው ቀዳማዊ አፄ ኃ/ሥላሴ በአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጣት ከሚቆጠሩት ሴት ተማሪዎች አንዷ ሆነው የመጀመሪያ ድግሪያቸውን አግኝተዋል።

ወ/ሮ ብርሄኔ ከልጅነታቸው ጀምሮ አብሮ ያደገው አንድ ባህሪያቸው የሕይወታቸውን መንገድ መርቶታል። ይህም ኢ-ፍትሐዊነት መጠየፋቸው ነው።

ምንም እንኳ አስገባሪ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ ቢያድጉም ለገባሪ ተቆርቋሪ ነበሩ። ይህ የልብ ትግላቸውም መስመር የያዘው ኑሯቸውን ከባለቤታቸው ጋር በመሠረቱበት ጄኔቭ ነው።

በስዊትዘርላንድ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ “የዓለምን አቀማመጥ ተረዳሁ። የኢ-ፍትሐዊነትን ሥርዓት/ስልተ መሠረት አጠናሁ” ሲሉ መፃፋቸው ላይ ገልፀውታል።

በተለይም ደግሞ “Missusing symbols” የተባለው ትምህርት በማኅበረሰቡ ቅቡልነት እና ከበሬታ ባላቸው ባህል እና ሃይማኖት በማሳበብ ለኢ-ፍትኃዊነት የተዘጋጀ መደላድል መሆኑን የተረዱበት ነው።

በመንግሥታቱ ድርጅት ስር ለፆታ እኩልነት እና ሴቶች መብት በሚሠራው አካል ውስጥ መሥራት ሲጀምሩ ደግሞ የሕይወታቸውን እኩሌታ ያሳላፉበትን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቆም የበኩላቸውን አበርክተዋል። አህጉራቸው አፍሪካ ላይ ስር የሰደደው ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ሽፋን የተጎናፀፈው የሴት ልጅ ግርዛትን ሊዋጉ ሲነሱ፤ ለዘመናት ሊቆይ በጽኑ መሠረት ላይ የተቀረፀ የመሰለው ሥርዓት፣ አስተሳሰብ፣ ባህል እጁን ዘርግቶ አልተቀበላቸውም። ይልቁንም አፍ አውጥቶ ተሟገታቸው፤ ፈተናቸው። እርሳቸውም የዋዛ አልነበሩም እና ድርጅት መሥርተው፤ መሳሪያቸውን ስለው ብቅ አሉ።

ወ/ሮ ብርሃኔ በ1970ዎቹ መጨረሻ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ላይ የሚሠራውን ኢንተር አፍሪካ ኮሚቴ (Inter Africa committee) የተባለውን ድርጅት በመመሥረት ለ27 ዓመት ፕሬዝዳንት ሆነው መርተውታል።

ወ/ሮ ብርሃኔ ለጥንካሬያቸው ምንጭ “አንድ ነገር ብቻ አይደለም” ይላሉ። ዕድልን ትልቅ ስፍራ ቢሰጡም ከራሳቸው ጥረት ባልተናነሰ እናታቸው የመጀመሪያ አስተማሪያቸው በመሆን፤ አያታቸው ደግሞ በለጋ ዕድሜያቸው ለጋብቻ የሚቀርብ ጥያቄን በተደጋጋሚ በመመለስ ለስኬታቸው ያመሰግኗቸዋል።

ምንጭ- ቢቢሲ

 

(ማራኪ ሰውነት)

በኲር የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here