የጡት ካንሰር ህክምናን ስኬታማነት በእጥፍ የሚያሳድገዉ

0
14

ተመራማሪዎች በእንክብል መልክ የተዘጋጀ የቫይታሚን “ዲን” ተጨማሪ ምግብ የጡት ካንሰር ህሙማን በየእለቱ እንዲወስዱ ማስቻል  ከ “ኬሞቴራፒ” ህክምና በኋላ የመዳን ምጣኔያቸውን ካልወሰዱቱ በእጥፍ እንደሚያሳድገው ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ሰሞኑኑ አስነብቧል::

 

በብራዚል የሳኦፖሎ ተመራማሪዎች እድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆናቸው 80 ተመላላሽ የጡት ካንሰር ታማሚዎች በሁለት ቡድን ተከፍለው 40ዎቹ የተመጠነ የቫይታሚን “ዲ” ተጨማሪ እንክብል ቀሪዎቹ የ “ኘሌስቦ ታብሌት” ወስደው  “የኬሞቴራፒ” ህክምና ተሰጥቷቸዋል::

 

የ “ኬሞቴሯፒ” ህክምና  40 በመቶ የካንሰር እጢዎችን ለመቀነስ እና ለማስወገድ ከቀዶ ጥገና  በፊት የሚሰጥ ህክምና መሆኑም ተገልፆል:: ከስድስት ወራት ክትትል በኋላ በቡድኖቹ መካከል ጉልህ ልዩነት መገኘቱን ነው የደረሱበት – ተመራማሪዎቹ:: በውጤቱም ቫይታሚን “ዲ” የወሰዱት ከ “ኬሞቴራፒ” በኋላ የካንሰር ህመማቸው ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን አረጋግጠዋል:: “ኘሌስቦ” የወሰዱት የቡድን አባላት ደግሞ 24 በመቶ የሚሆኑት ከካንሰር ህመማቸው ተፈውሰዋል::

 

ቫይታሚን “ዲ” አካል “ካልሼየም” አና “ፎስፈረስን” እንዲሻ ይረዳል፤ በዚህም የአጥንት ጥንካሬን ይጠብቃል:: ከዚህ በበለጠም ካንሰርን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችን የመከላከል ዓቅምን ያሳድጋል:: ቫይታሚን “ዲ” በዋናነት ከፀሀይ ብርሃን የሚገኝ ቢሆንም ከተወሰኑ የመግብ ዓይነቶችም ሊገኝ እንደሚችል ነው የተጠቆመው::

በመጨረሻም ቫይታሚ “ዲ” የጡት ካንሰር የ “ኬሞቴራፒ” ህክምናን ውጤታማነት ለማሻሻል ከሚጠቅሙ ሌሎች መድሃኒቶች ጋር ሲነፃፀር ተደራሽ እና በቀላሉ በአነስተኛ  ወጪ የሚገኝ አማራጭ መሆኑ ነው በማጠቃለያነት ለንባብ የበቃው::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here