የበካይ ኘላስቲክ ማስወገጃ

0
16

በአሜሪካ የሚዙሪ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በውኃ ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን በካይ የኘላስቲክ ቅንጣቶችን አጣብቆ መያዝ የሚችል አዲስ የአልጌ ዝርያ መፍጠራቸውን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል፡፡

ተመራማሪዎቹ በስነህይወታዊ ምህንድስና ሙከራ አግኝተው ያስተዋወቁት የአልጌ ዓይነት ከተለምዷዊው የአልጌ ዓይነት በተለየ በሚያመነጨው “ሊሞኔን” የተሰኘ የብርቱካን ሽታ ያለው ዘይት ቅንጣት ኘላስቲኮችን አጣብቆ የሚያስቀር ነው፡፡

ኘላስቲክ ቅንጣቶቹ ከውኃ አካላት ለአብነት ከኩሬ፣ ሀይቆች፣ ወንዞች ወዘተ ውስጥ  በዓሳዎች ተበልተው  ሰዎች ዓሳን ሲመገቡ ወደ አካል ሊገቡ እንደሚችሉ ጠቁመዋል -ዋና ተመራማሪዋ ሱዚዳይ፡፡

ተመራማሪዋ እስከ አሁን ከየመኖሪያ አካባቢዎች መጠናቸው ከፍ ያሉ ኘላስቲኮችን ለማሰባሰብ እና ለማስወገድ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው የጠቀሱት፤ በሌላ በኩል መጠናቸው ያነሰ ወይም ደቂቅ የኘላስቲክ ቅንጣቶች በየውኃ አካላት፣ በተለያዩ ስነ ምህዳሮች ተሰራጭቶ መገኘቱ ከፍተኛ የብክለት መንስኤ መሆኑንም ነው ያሰመሩበት፡፡

የኘላስቲክ ቅንጣቶቹን አጣብቆ እና ሰብስቦ የሚይዘውን የአልጌ ዓይነት በመገልገል ውኃውን  አጣርቶ ለመጠጥነት ማዋል አንደኛው ጠቀሜታ ሲሆን ሌላኛው የተሰበሰበውን ደቂቅ ኘላስቲክ አውጥቶ ለሌላ ምርት በግብአትነት ማዋል እንደሚያስችልም ነው ያብራሩት -ተመራማሪዋ፡፡

ተመራማሪዋ በቀጣይ በምርምር የተገኘውን የአልጌ አይነት በስፋት አምርቶ  በውኃ ማጠራቀሚያ ውስጥ በማኖር ብክለትን ማስወገድ እንደሚቻል አረጋግጠዋል፡፡

በመጨረሻም “shrek’’  የሚል ቅፅል ስም በተሰጠው 1000 ሊትር ውኃ  በሚይዝ “ባዮ ሪአክተር” ወይም ማብላያ ውስጥ መሞከራቸው ነው በማጠቃለያነት ለንባብ የበቃው፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 17   ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here