ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
27

በምዕ/ጉጃም ዞን የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል የሚገኘውን የተለያዩ ቢቢኤም ማረሻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁጥር ከ1-3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ዋናውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ፤ ሆናም ግን ብረታ ብረቶቹን በአካል ማየት ከፈለጉ ቡ/ዙ/ወ/ ግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ  ማስከበሪያ  የሞሉትን ጠቅላላ  ዋጋ  አምስት በመቶ በባንክ  በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ  ሲፒዩ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ  አለባቸው ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 17/2018 ዓ.ም  እስከ  ሰኔ 1/2018  ዓ.ም ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በሆነ በታሸገ ፖስታ ዋና እና ፎቶ ኮፒውን ቡ/ዙ/ወ/ገ/ ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ ቡድን በተዘጋጀው  የጨረታ ሳጥን  ዘወትር በስራ ሰዓት  እስከ ሰኔ 1/2018 ዓ.ም   ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች  የጨረታ  ሃሳቡን  ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት  የአንዱን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመውሰድ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ሰነዱን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት  ግዥ/ን/አስ/ ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. አሸናፊው ድርጅት  ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ  ጠቅላላ ዋጋ  10 በመቶ  በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ  (ሲፒዩ ) ወይም  በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ   የባንክ ዋስትና  ማቅረብ አለባቸው፡፡
  13. በጨረታው  ለመሳተፍ የሚፈልጉ  ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ን/አስ/ ቡድን በአካል በመገኘት  ወይም  በስልክ ቁጥር 058 774 0237 በመደወል ማግኘት  ይችላሉ፡፡
  14. ሌሎች በጨረታ ማስታወቂያው ያልተካተቱ ሃሳቦች በግዥ መመሪያችን ቁጥር 1/2003 እና በሌሎች በተሻሻሉ የግንባታ የግዥ መመሪያዎች  የምንገዛ ይሆናል፡፡

የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here