ቁጥር የሠ/ቅ.ማ/3150/2018
ቀን 13/09/2018 ዓ/ም
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ያሉትን ክፍት የስራ መደቦች ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ ስራ ፈላጊዎች መካከል በቋሚ ቅጥር አወዳድሮ በመቅጠርና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
| ተቁ | የሥራ መደቡ መጠሪያ | ደረጃ | የመ/መ/ቁ | ደመወዝ | ብዛት | ዳይሬክቶሬት/ዝግጅት | የሥራ ቦታ | ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት | ተፈላጊ የስራ ልምድ |
| 1 |
የአረብኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሪፖርተር 2 |
12 | አሚ-1525
|
በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት | 01 | አዲስ አበባ ኅብር ዝግጅት | አዲስ አበባ | በብሮድካስት ጋዜጠኝነት፣ በጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣ በተግባቦት (ኮሙኒኬሽን)፣ በስነ-ጽሁፍ፣በቋንቋ፣ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በተዛማጅ የትምህርት መስክ የሰለጠነ | · የመጀመሪያ ዲግሪና 3 ዓመት ወይም ሁለተኛ ዲግሪ
1 ዓመት አግባብንት ያለው/ት የስራ ልምድ · ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ የአረብኛ ቋንቋ መስማት፣ መናገር፣ ማንበብና መጻፍ የሚችል/የምትችል |
| 2 | የአፋርኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሪፖርተር 2 | 12 | አሚ-1500
|
በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት | 01 | አዲስ አበባ ኅብር ዝግጅት | አዲስ አበባ | በብሮድካስት ጋዜጠኝነት፣ በጋዜጠኝነትና ተግባቦት፣ በተግባቦት (ኮሙኒኬሽን)፣በስነ-ጽሁፍ፣ በቋንቋ፣ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በተዛማጅ የትምህርት መስክ የሰለጠነ | · የመጀመሪያ ዲግሪና 3 ዓመት ወይም ሁለተኛ ዲግሪ
1 ዓመት አግባብነት ያለው/ት የስራ ልምድ · ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ የአፋርኛ ቋንቋ መስማት፣ መናገር፣ ማንበብና መጻፍ የሚችል/የምትችል |
ማሳሰቢያ፡-
- የምዝገባ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
- አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ፣ የትምህርት ማስረጃቸውን ኦርጅናል ከማይመለስ ኮፒ ጋር ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አመልካቾች በእምነት ማጉደል ፣በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከተጠቀሰዉ አግባብነት ያለው የትምህርት ዝግጅት ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
- አመልካቾች መልካም ስነ-ምግባር ያላቸው፣ ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዱ፣ጥሩ ስብዕና ያላቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የትምህርት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሙያ ብቃት ምዘና ያልተጀመረባቸው የትምህርት መስኮች ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- በግል የተሰራባቸው የስራ ልምደች የስራ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ከገቢዋች ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከአንድ የስራ መደብ በላይ መመዝገብ አይቻልም፡፡
- የፈተና ቦታና ፈተና የሚሰጥበት ቀን በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
- አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታ ameco.et ማግኘት ትችላላችሁ ወይም ይህ ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ https://forms.gle/ijtUjSyLbEokqr1y8 መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር

