ቁጥር የሠ/ኮ.ቅ.ማ/3148/2018
ቀን 13/09/2018 ዓ/ም
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ ስራ ፈላጊዎች መካከል በጊዜያዊ የረጅም ጊዜ (በኮንትራት) ቅጥር አወዳድሮ በመቅጠር ማሰራት ይፈልጋል፡፡
| ተቁ | የሥራ መደቡ መጠሪያ | ደረጃ | የመ/መ/ቁ | ደመወዝ | ብዛት | የሥራ ቦታ | ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት | ተፈላጊ የስራ ልምድ |
| 1. | የግዢ ባለሙያ 2
|
IX | አሚ-1684 | በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሠረት | 01 | አዲስ አበባ ቅርንጫፍ | በግዢና የአቅርቦት ሰንሰለት፣ ስራ አመራር፣ በኢኮኖሚክስ፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በቢዝነስ አስተዳደርና በተዛማጅ የትምህርት መስክ | · የመጀመሪያ ድግሪ 1 ዓመት አግባብ ያለው የስራ ልምድ |
ማሳሰቢያ፡-
- የምዝገባ ቀን ማስታወቂያው በበኩር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
- አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አመልካቾች በእምነት ማጉደል፣ በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ኦርጅናሉን የትምህርትና የስራ ልምድ ለተጠየቀበት መደብ ብቻ የስራ ልምዳቸውን መረጃ ኦርጅናል ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከተጠቀሰዉ አግባብነት ያለው የትምህርት ዝግጅት እና የስራ ልምድ ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
- አመልካቾች መልካም ስነ-ምግባር ያላቸው፣ ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዱ፣ጥሩ ስብዕና ያላቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የትምህርት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሙያ ብቃት ምዘና ያልተጀመረባቸው የትምህርት መስኮች ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- የኮንትራት ቅጥሩ ለ6 ወር ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በየ6 ወሩ ይታደሳል፡፡
- በግል ተቋማት የተሰራባቸው የስራ ልምዶች የሰራ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ ይገባል፡፡
- ተወዳድረው ያለፍ የስራ ተያዥ ወይም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
- አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታችን ameco.et ማግኘት ትችላላችሁ ወይም ይህ ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ https://forms.gle/DmxUASmvKoQqxCbF9 መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 5007 ባህር ዳር ይደዉሉ፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባሕር ዳር

