ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
25

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘዉ የጎህ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተወሰነ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን ሎት 1. ስሚንቶ ፒፒሲ ብዛት 900 ኩ/ል፣ ሎት 2. አሸዋ 144 ሜ/ኩብ፣ ሎት 3. ጠጠር 002 208 ሜ/ኩብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት (ግለሰብ) መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በጎሕ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ (ቫት) የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን አይነት፣ መጠንና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) የሚገልጽ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከጎህ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ ቀርበው በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-4 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት በ3 ቀን ዉስጥ ያሸነፈበትን የግንባታ ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. አሸናፊው የሚለየው በሎት (በምድብ) ዋጋ ይሆናል፡፡ ከሎት ውስጥ የአንዱን ዕቃ ዋጋ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን እስከ 6፡30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10 ኛው ቀን መጨረሻ ከቀኑ 8፡30 ላይ ታሽጎ  በዚሁ እለት 8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. ዪኒየኑ ከሚገዛው ዕቃ ውስጥ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
  10. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 ደዉለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ /ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here