የምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ከመደበኛ በጀት ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ እህል፣ የባልትና ዉጤቶችን እና መድሃኒት አጫርቶ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን ሎት1 1.ቀይ ጤፍ፣ 2. በቆሎ፣ 3. ነጭ ሌሌ ማሽላ፣ 4. ጅሁላ ማሽላ፣ 5. ደበር ማሽላ፤ ሎት2. የባልትና ዉጤቶችን 1. የተዘጋጀ ሽሮ፣ 2. የምግብ ዘይት፣ 3. የምግብ ጨዉ፣ 4.እርሾ፣ 5. ጎመን ዘር እና ፊኖ ዱቄት፤ ሎት3. መድሃኒት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ የሆነዉን አቅራቢ ድርጅት ለ12 ወር ማለትም ከሀምሌ 1/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/ 2019 ዓ.ም ዉል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የሚገዙ የእህል፣ የባልትና እና የመድሃኒት አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእህል፣ የባልትና እና የመድሃኒት ዉጤቶች 1.5 በመቶ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመሂ 1 ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከግንቦት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 8/2018 ዓ.ም ድረስ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ዉሃ ማረሚያ ቤት መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በመቅረብ ከ1 እስከ 3 ያሉ ሰነዶችን የማይመለስ 50 ብር በመክፈል መዉሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ከ1 እስከ 3 የተዘረዘሩት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ከ15 ቀን ቆይታ በኋላ በ16 ኛው ቀን ማለትም ሰኔ 8/2018 ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ዉኃ ማረምያ ቤት መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልፅ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ስለሆነ ሁሉንም በሎት 1. የተቀመጠዉን የእህል ዋጋ እና በሎት 2. የተቀመጠዉ የባልትና ዋጋ በሎት 3 የተቀመጠዉን መድሃኒት ለየራሳቸዉ መሙላት አለባቸው፡፡ ካልተሞሉ ግን ከጨረታ ወጭ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የእህል፣ የባልትና እና የመድሃኒት ዉጤቶች ምዕ/ጎ/ዞን ገ/ዉሃ ማረሚያ ቤት ንብረት ክፍል በዝርዝሩ መሰረት ማስረከብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞላ ዋጋ እንዲሁም የማይነበብ ስርዝ ድልዝ አንቀበልም፡፡
- መ/ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ የምግብ እህል አቅርቦት 20በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ፣ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 327 0163 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ በምዕ/ጎ/ዞን ዐቃቢ ህግ መምሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ገ/ዉሃ ማረምያ ቤት መምሪያ

