የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
28

አውራ አምባ ማ/ፋ/ኢ/አ/ማ እነ አቶ ግዛቸው አጥናፍ የተበደሩትን ገንዘብ ባለመክፈላቸው ለብድሩ መያዣ የሆነውን ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሠረት ሰኔ 25/2018 ዓ.ም በግልጽ ጨረታ በሐራጅ ይሸጣል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች የቤቱን ይዞታ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መመልከት ይችላሉ፡፡

የተበዳሪ ስም የንብረቱ ባለቤት የካርታ ቁጥር የቦታው ስፋት የግንባታ ደረጃ አድራሻ ቀበሌ የጨረታው መነሻ ዋጋ የጨረታው ቀንና ሰዓት
ቀን ሰዓት
እነ ግዛቸው አጥናፍ ወ/ሮ ዙፋን ብርሃኔ አፄቴ/11279/16 250 ካ.ሜ መኖሪያ ቤት G+2 ስላብ የተሞላና ኮለን የተሰራ ባሕር ዳር አፄ ቴዎድሮስ ክ/ከ ማራኪ ልዩ ቦታ አርሴማ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ 5,303,562 ሰኔ/25/2018 ዓ.ም 3፡00-5፡00

 

የጨረታ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ዕለት የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ የቤቱን ግምት 15 በመቶ በባንክ የተመሰከረ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
  2. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት፡፡
  3. በሐራጁ ላይ መገኘት የሚችሉት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ ተበዳሪ፣ ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸውና የተመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው፡፡ ተበዳሪና ተወካዮቻቸው ባይገኙም በሌሉበት ጨረታው ይካሄዳል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ ለሆነው ተጫራች በማይክሮ ፋይናንሱ የብድር ፖሊሲ መመሪያና ቅድመ ሁኔታ መሰረት ብድር ሊመቻች ይችላል፡፡
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በጨረታው የመጨረሻ 30 ደቂቃ ውሰጥ የተጫራቾች ምዝገባ አይካሄድም፡፡
  6. የሐራጁ አሸናፊ/ ገዥ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ከስም ማዛወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የግብር ግዴታዎችን ገዥው ይከፍላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታው ቀን ከመድረሱ 5 (አምስት) ቀን በፊት ከማይክሮ ፋይናንሱ ጋር በመነጋገር በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዘው ለጨረታ የቀረበውን ንብረት መጎበኘት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ነው፡፡
  9. ጨረታ የሚከናወነው የተቋሙ ዋና መ/ቤት ቢሮ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ነው፡፡
  10. አጫራቹ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለተጨማሪ መረጃ 09 18 31 72 97 እና 09 18 79 00 03 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አውራ አምባ ማ/ፋ/ኢ/ኦ/ማ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here