የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለመግዛት ካቀደቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ውስጥ 1ኛ. ዲሰክቶፕ ኮምፒዩተር በቁጥር 02፣ ላፕቶብ በቁጥር 01 እንዲሁም ፍለሽ በቁጥር 15 በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ያቀረቡት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የኤሌክትሮኒክ እቃዎች የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግዥው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት የሚቻል ሲሆን የሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ነው፡፡
- በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ብር 6,000 (ስድስት ሽህ ብር) በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዝበን ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሳጥን በግዥ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ይገኛል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 14 ይገኛል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡ ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የእያንዳንዱን ሎት ሁሉንም ዝርዝር ያልሞላ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ የሞላበትን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስት ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመጨረሻው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው 2014 ዓ.ም የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ያወጣውን አዲስ የተሻሻለ የግዥ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 00 58፣ 058 141 00 91 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

