ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
12

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የህክምና እቃ አዉቶክሌቭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. ተጫራቾች እቃዎችን ወይም አገልግሎቾችን ለማቅረብ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ  የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማረኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
  8. በዚህ ጨረታ መጫረት የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው በተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድ ቅዳሜና በዝግ ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠየቀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚመለስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. አንድ ተጫራች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውን ላወጣው መስሪያ ቤት በፁሁፍ ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 03 30 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤትም የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡

የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here