የባሕር ዳር ከተማ አስተዳዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ለህግ ታራሚዎች ለምግብነት የሚዉሉ የተለያዩ በሎት የተገለጹ ግባቶችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት 1. የባቄላ ክክ፣ ሎት 2. ምጥን ሽሮ፣ ሎት 3. ምጥን በርበሬ፣ ሎት 4. ምስር ክክ፣ ሎት 5. የፋብሪካ ውጤት፣ ሎት 6. የአትክልት ዘይት፣ ሎት 7 ስኳር፣ ሎት 8. ማገዶ እንጨት፣ ሎት 9. ፊኖ ዱቄት፣ ሎት 10. አትክልት፣ ሎት 11. የቅባት እህል እንዲሁም ሎት 12. በቆሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፍርቶች ማሟላት የምትችሉ ተወዳዳሪዎች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸዉና ከመንግስት ሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ ለመሆናቸዉ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ሽያጭ ለሚፈጽሙ አቅራቢዎች (ቫት) ከማይጠየቅባቸዉ ዉጭ ባሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸዉ ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
- ተጫራቾች በስራ ፈቃዳቸዉ መሰረት ማቅረብ የሚገባቸዉን ለይተዉ በመሙላት በታሸገ ፓስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዉስጥ ከጨረታ መክፈቻዉ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር ባቀረቡባቸዉ የምግብ ግብዓቶች የገንዘብ መጠን ልክ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1. ብር 50,000፣ ሎት 2. ብር 50,000፣ ሎት 3. ብር 50,000፣ ሎት 4. ብር 50,000፣ ሎት 5. ብር 50,000፣ ሎት 6. ብር 50,000፣ ሎት 7. ብር 50,000፣ ሎት 8. ብር 100,000 ሎት 9. ብር 100,000፣ ሎት 10. ብር 10,000፣ ሎት 11 ብር 3,000 ሎት 12. ብር 100,000 በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረበ አለባቸው፡፡ አሸናፊዉ ዉል ሲይዝ የዉል ማስከበሪያ በጨረታ ማስከበሪያ ላይ ገንዘብ በመጨመር የሚያስዝ ሆኖ ለተሽነፈ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ ለሆነ ሽያጭና የሽያጭ ታክስ ከሚከፈለዉ ጠቅላላ ገንዘብ ላይ በመመሪያዉ መሰረት 3 በመቶ መክፋል ይኖርባቸዋል፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየትና በተለያዩ ፖስታ በማሽግ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና የድርጅታችዉን ማህተም ማሳረፍ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ዉጤቱ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ በማስያዝ ዉል ይዞ ያሸነፋባቸዉን ባ/ዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ጨረታዉ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ውሎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግዥ ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በ16ኛዉ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ መምሪያው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ሲሆን ሰባታሚት ማረ/ቤት በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 320 31 39 ደውለው ወይም በአካል ባ/ዳር ማረ/ቤት መምሪያ ግዥ/ፋን/ንብ/አስ/ስራ ሂደት በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ

