የኦቲዝም ዓይነቶች

0
6

ዓለም አቀፍ የተመራማሪዎች ቡድን በተለያዩ የአንጐል ግንኙነቶች ሊገለጹ የሚችሉ ሁለት የኦቲዝም ዓይነቶችን መለየት የሚያስችል ማስረጃ ማግኘቱን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስንብቧል፡፡

የጣሊያን ቴክኖሎጂ ተቋም በመረጃ ምንጭነት ለንባብ እንዳበቃው ዓለም አቀፉ የተመራማሪዎች ቡድን በአንጐል ውስጥ በተለያዩ የግንኙነት ስልቶች ሊገለጹ የሚችሉ “ሀይፐርኮኔክቲቪቲ” እና “ሀይፓከኔክቲቪቲ” የተሰኙ ሁለት የ “ኦቲዝም” ዓይነቶችን በጥናት እና ምርምር መክፈል በሚያስችል ማስርጃ አረጋግጧል፡፡

ተመራማሪዎቹ ዓይነቶቹን በውል ለመለየት 940 በ “ኦቲዝም” የተያዙ የታዳጊዎች እና የወጣቶችን የአንጐል ምስል “ስካን” በማድረግ ተንትነዋል፡፡ ከትንታኔ ውጤታቸውም  “ሀይፐር ኮኔክቲቪቲ” በሚል የተለየው በአንጐል ክልሎች መካከል የግንኙነት መጨመር ወይም መፍጠንን ያመላከተ ሲሆን “ሀይፓኮኔክቲቪቲ” በአንጐል ክልሎች ያለው ግንኙነት የቀነሰ ወይም አዝጋሚነትን የሚያሰፍን መሆኑን ነው ያረጋገጡት፡፡

በተመራማዎቹ ቡድን ውስጥ የተካተቱት ዶክተር አሌሳንድሮ ጎዚ እስከአሁን ወይም ከዚህ ቀደም በጤናው መስክ በነበረው ሂደት ሁለቱን የ “ኦቲዝም” ዓይነቶች በውል መነሻ እና ሂደታቸውን ያመላከተ በጥናት እና ምርምር ላይ የተመሰረተ ማስረጃ አለማግኘታቸውን ነው ያሰመሩበት-ይህ በመሆኑም ጥናት እና ምርምሩን መከወን ግድ ብሏቸዋል፡፡

ቡድኑ ከሁለቱ  የ “ኦቲዝም” ዓይነቶች “ሀይፐር ኮኔክቲቪቲ” በሚል የተለየው የጤና እክልነቱ ወይም ክብደቱ ከፍ ያለ መሆኑን ገልጾ ግኝቱ በ “ኦቲዝም” ለተጠቁ ምርመራ፣ እንክብካቤ አና ህክምናን በግላዊ አቀራረብ ለመዘርጋት እንደሚረዳ ነው በማጠቃለያነት ያሰፈረው፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሰኔ 8  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here