ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ  ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
17

በደቡብ ጎንደር ዞን የሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በሀሙሲት ከተማ ቀጠና 01 አውራ ጎዳና ላይ ቀጠና 04 ጎህ ት/ት ቤት ላይ፣ ሀሙሲት ፖሊስ ጣቢያ ላይ እንዲሁም ሀሙሲት መዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ያሉ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. ማንኛውም የመግዛት አቅም ያለው ተጫራች መጫረት ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ማንነቱን የሚገልጽ ዲጂታል መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  3. የእቃዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከረዳት ገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ናሙናዎቹን ከላይ በተገለጸው አድራሻ ማየት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በቁርጥ ብር 150,000 (አንድ መቶ አምሳ ሽህ ብር) በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000433908997 ወይም በአባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 4502117448491016 በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ያስያዙትንም የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  6. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡንና ማስረጃዎችን ዋናዉን በጥንቃቄ በታሸገ በአንድ ፖስታ ለሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ተብሎ ተጽፎበት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 16ኛዉ ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የሚታሸገውም በዚሁ ሰዓት ይሆናል፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በገንዘብ ጽ/ቤት በ16ኛዉ ቀን 4፡00 በጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊዉ ማሸነፉ ከተገለጸለት ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ዉስጥ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርቦ የውል ማስከበሪያ በቁርጥ ብር 350,000 (ሶስት መቶ አምሳ ሽህ ብር) በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000433908997 ወይም በአባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 4502117448491016 በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ዉል መዉሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ዉል ካልወሰደ በግዥ መመሪያዉ መሰረት አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፡፡
  9. የሚሸጡ ብረታ ብረቶች የሚቀርበዉና ርክክብ የሚፈጸመዉ አይነቱና መጠኑ ከተረጋገጠ በኋላ በሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ሃሙሲት ከተማ ላይ ይሆናል፡፡
  10. የጨረታ መክፈቻዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊዉ የሚለየዉ ለሁሉም ዕቃዎች በሰጠዉ ከፍተኛ ዋጋ የሚወስን ሲሆን በሰነዱ የዋጋ መሙያ ቦታ ላይ የአንዱንም እቃ ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  12. ከዋጋ ጥናቱ በታች የሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ማንኛውም የአስተዳደርም ሆነ የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፈነው በተጫራቹ በኩል ብቻ ይሆናል፡፡
  15. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ ሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 53 10 53 ደዉለዉ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሀሙሲት ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here