በአፈ/ከሣሽ አንዱአለም ብርሄ እና በአፈ/ተከሣሽ እነ መ/ታ ተሰራ ቀፀላ /18/ ሰዎች መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳዩ 1ኛ. ንብረትነቱ የስምተኛ ተከሣሽ /የአቶ ፈንታ ሞገስ ቤት የሆነውን በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ አዋሣኝ በምሥራቅ ክፍት ቦታ፣ በምዕራብ አሸናፊ ሞላ፣ በሰሜን የመኪና መንገድ እንዲሁም በደቡብ ክፍት ቦታ የሚያዋስነውን ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋ ብር 1,345,348 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አምስት ሽህ ሶስት መቶ አርባ ስምንት ብር/ በጨረታ ይሸጣል፡፡ 2ኛ. በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ አዋሣኝ በምሥራቅ ፀጋዩ የተዋለ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን አስቻለ መኩሪያ እንዲሁም በደቡብ ትዕዛዙ አቸነፍ የሚያዋስነውን ንብረትነቱ የአስራ አንደኛ ተከሣሽ የአቶ አወቀ አልማው የሆነውን ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,183,290 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማኒያ ሶስት ሽህ ሁለት መቶ ዘጠና ብር) በጨረታ የሚሸጥ ይሆናል፡፡ 3ኛ. በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሣኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ያለምወርቅ ተገኘ፣ በሰሜን ያለምወርቅ እንዲሁም በደቡብ ጠጀ ታየ የሚያዋስነውን እና ንብረትነቱ የአሰራ አራተኛ ተከሣሽ የአቶ የኔው ፀጋ የሆነውን ቤት መነሻ ዋጋ ብር 1,441,784 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ አርባ አንድ ሽህ ሰባት መቶ ሰማኒያ አራት ብር) በማድረግ ጨረታውን ከሰኔ 10/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ በማዋል ጨረታው ሐምሴ 11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ቤቶቹ በሚገኙበት ቦታ በማጫረት በወቅቱ የጨረታ አሸናፊው ከተገኘም 1/4ኛውን ወዲያውኑ በከፍ/ፍ/ቤቱ የአማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9900017292928 በሆነ ገቢ እንዲያደርግ እና ቀሪውን ደግሞ በቀጠሮው ቀን ይዞ እንዲቀርብ በማድረግ በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቦታው ተገኝተው መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡
የአዊ /ብሔ/ዞን/ ከፍ/ቤት

