ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
12

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጥበቃ አውትሶርስ የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች ለመግዛት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች በኮርፖሬሽናችን ስም የተሰራ (ሲፒኦ) ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል /Unconditional Bid bond guarantee/ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡ አሸናፊው ከተለየና ውል ከተፈረመ በኋላ ላላሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 1,000 (አንድ ሽህ ብር) ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ለተገለፀው የጥበቃ አውትሶርስ የአገልግሎት ግዥ የሚያቀርቡትን ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ለግልገል አባይ ማሻሻያና ማስፋፊያ የመስኖ ልማት ግንባታ ለዋናው ካምፕ፣ ሄድ ወርክ ጠጠር እና አሽዋ መፍጫ ክሬሸርና ሳንድ ሜከር የቦር ሆል (የንፁህ መጠጥ ውሀ ጥልቅ ጉድጓድ)፤ ለተለያዩ ቦታዎች ያሉ ሶስት ካምፖች እና ፕሮጀክቱ ወደ ስራ ሲሰማራ በየሳይቱ የሚሰማሩ ማሽነሪዎች ኢኩፕመንት እና የተለያ ግብዓቶችን የሚጠበቁ ሲሆን ያለውን ዋጋ ስድስት (6) በድምር ዋጋ የምናወዳድር ይሆናል፡፡
  6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ማድረግ አይቻልም ካለ ግን ዋጋውን በሞላው አካል መፈረም ይኖርበታል፡፡ በሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም ፊርማ እና ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው /ሃያኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
  9. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 22 14 79 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here