አፈ/ከሳሽ ደሴ አንጀት እና በአፈ/ተከሳሽ እነ ሀ/ማሪያም አላምረው 2ቱ ራሳቸው መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ 006፣ በምዕራብ 008፣ በሰሜን 003 እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው በ1ኛ አፈ/ተከሳሽ በሀ/ማሪያም አላምረው ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የድርጅት ቤት መነሻ ዋጋውን ብር 6,985,171 (ስድስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሰባ አንድ ብር) ተደርጎ የጨረታ ማስታወቂያው ሰኔ 10/2018 ዓ/ም እስከ ሀምሌ 07/2018 ዓ/ም ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ሀምሌ 08/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ይከናወናል ሲል ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን (በሲፒኦ) ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

