ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1. በቆሎ ሽያጭ፣ ሎት 2. ጤፍ ሸያጭ፣ ሎት 3. ሩዝ ሽያጭ እንዲሁም ሎት 4. የዱቄት ማበልጸጊያ  ማሽን ግዥ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ብቻ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ (ዋስትና) ወይም (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙን ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ዋጋ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  1. ተጫራቾች  አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  1. ተጫራቾች  በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ክብ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በፖስታው ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ሀምሳ ብር ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው የሚቆየው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል፡፡
  4. ቅዳሜ ለዩኒየኑ የሥራ ቀን ቢሆንም ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  6. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  7. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን የንግድ ፈቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ከሎት አንድ ወጭ ያሉትን ግን ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት ይችላሉ፡፡
  8. አሸናፊው ያሸነፈዉን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ የሚያቀርብ ሲሆን ማንኛዉም ወጭ አሸናፊዉ ይሸፍናል፡፡
  9. የሚገዙትን ሆነ የሚሽጡ ማንኛዉም እቃዎች መጠንና (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊዉ የሚለየዉ በተናጠል ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ግዥዎች /ሽያጭ/ በፍትህ ዉሉ ከተመረመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊዉ ይከፍላል፡፡ ሰብሉን ለማንሳት የሚያሰፈለጉ ማንኛውም የወዛደር ማሰጫኛ እና የትራንሰፓርት ወጭዎች አሽናፊ የሚሽፍን ይሆናል፡፡
  11. ሰብሉ የሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዘን ሲሆን ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት ይችላሉ፡፡
  12. በዚህ ያልተጠቀሱ ሃሳቦች ቢኖሩ በህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  13. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /09 11 55 36 53 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here