በሰሜን ጎጃም ዞን የሰሜን አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት G+4 የቢሮ ግንባታ እንዲገነባላቸው በጠየቁን መሰረት ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወይም ህንፃ ስራ ተቋራጭ ያላቸውን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘንብ በመሂ 1 ከሰሜን አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ላይ በመክፈልና የከፈሉበትን ማስረጃ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከሰኔ 02/2018 ዓ.ም እስከ 21/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ ይቆያል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ተሽጦ በ22ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሲመጡ የንግድ ሥራ ፈቃዳቸውን የጨረታ ሰነድ ለሚሸጠው አካል ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ኦርጅናል እና ኮፒ የመጫረቻ ሰነዶችን ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን በሰሜን አቸፈር ወረዳ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ 05 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ስለሆነ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚገኙትን የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ እና የሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልጻፉ ግን የተሞላው ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከሰ/አቸ/ወ/ግ/ን/አስ/ቡድን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ ሁሉን የጨረታ ሰነዶች ፖስታው ላይ በማስገባት ማሸግ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሥርዝ ድልዝ በማድረግ አይቻልም፡፡ የራሳቸውን ፊርማ ቢያስቀምጡም በመመሪያ ማሻሻል ምክንት ያንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ የራሳቸውን ፊርማ ቢያስቀምጡም ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋውን ላለመሰረዝ በጥንቃቄ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ በውድድሩ ወቅት 3 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ሲከፈት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲክ ቼክ/ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት ሲኖረው ከዚህ የበለጠ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ በውድድሩ ከ3 በታች ከሆኑ ሲከፈት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲክ ቼክ/ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ አንድ በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት ሲኖረው ከዚህ የበለጠ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ እንዲሁም ተጫራቾች ቴክኒክልና ፋይናንሻል ዶክመንቶችን በተለያዩ ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዩች በግዥ አፈጻጸም መመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡
የሰሜን አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

