የጨረታ ዙር 3ኛ/2018 ዓ.ም
ጨረታው አይነት /መደበኛ
- የሻሁራ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለመኖሪያና ለድርጅት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የሚፈልጉ ሁሉ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሰኔ 22/2018 እስከ ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፍል ሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 27 ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከሰኔ 22/2018 እስከ ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም ነው፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ቦታውን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ሰኔ 27፣29 እና ሐምሌ 02 መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሐምሌ 3/2018 ከረፋዱ 3፡00 በሻሁራ ከተማ አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የማራዘም እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 32 75 06 77 ወይም 09 18 13 81 73 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሻሁራ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የመሬት ሊዝ ጨረታ የቦታዎች ዝርዝር መረጃ
| ተ.ቁ | አገልግሎት | የሚገኝበት ቀጠና | የሚገኝበት ቀበሌ | ብሎክ ቁጥር | ፕሎት ቁጥር | ስፋት በካ.ሜ | መነሻ ዋጋ | ጠቅላላ ዋጋ | የግንባታው ደረጃ |
| 1 | መኖሪያ | ቴዎድሮስ | 02 | 108 | ጨመ-04 | 150 | 500 | 75,000 | G+0 |
| 2 | መኖሪያ | ቴዎድሮስ | 02 | 108 | ጨመ-03 | 150 | 500 | 75,000 | G+0 |
| 3 | መኖሪያ | አንድነት | 01 | 104 | ጨመ-973 | 150 | 500 | 75,000 | G+0 |
| 4 | መኖሪያ | አንድነት | 01 | 104 | ጨመ-972 | 150 | 500 | 75,000 | G+0 |
| 5 | መኖሪያ | አንድነት | 01 | 104 | ጨመ-971 | 150 | 500 | 75,000 | G+0 |
| 6 | ድርጅት | አንድነት | 01 | 107 | ጨድ-01 | 300 | 800 | 240,000 | G+4 |
| 7 | ድርጅት | አንድነት | 01 | 107 | ጨድ-02 | 300 | 800 | 240,000 | G+4 |
መግለጫ
ጨድ፡- ለጨረታ የቀረበ የድረጅት ቦታ ማለት ነው፡፡
ጨመ- ለጨረታየቀረበ የመኖሪያ ቦታ ማለት ነው፡፡
የሻሁራ ከተማ /አስ/መሬት ጽ/ቤት

