አውራ ጐዳናዉ

0
7

በቻይና ደቡብ ምእራብ ቾንግኪንግ ግዛት ከቀሪው ዓለም ተነጥለው ሲኖሩ የነበሩ 23 የላንዩንግ መንደር ቤተሰቦች ከመገናኘት ያገዳቸውን የላንዩንግ አለታማ ኮረብታን ከባህር ወለል 914 ሜትር ከፍታ ላይ አንድ ነጥብ ሁለት ኪሎ ሜትር የሚረዝም የመኪና መንገድ በእጅ መሣሪያ ጠርገው መስራታቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

የቀላል ተሽከርካሪ መጓጓዣ መንገዱን በመጥረቡ ሂደት የእያንዳንዱ ቤተሰብ አባል 80 የሚሆኑቱ መሳተፋቸው ነው የተገለፀው፡፡ ለመንገዱ ጠረጋም በእጅ መሣሪያ መሮ እና መዶሻ በመቦርቦር እና በመቁረጥ ጠርገው ለማጠናቀቅ አራት ዓመታት ፈጅቶባቸዋል፡፡

የቀላል ተሽከርካሪ መንገዱን ለመጥረግ የግንባታ ማሽን ወይም “ኤክስካቫተር” እና “ሎዲር” የመሳሰሉትን ለመገልገል የግንባታ ቦታው ምቹ አለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡  ቀጣናውን በሚያስተዳድሩ ኃላፊዎችም ሁነቱ ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሳይከናወን መቆየቱን ድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ከሁሉም በላይ ለተሽከርካሪ ምቹ የሆነ አውራ ጐዳና አለመኖር ተነጥለው በነበሩት የላንዩንግ መንደር ኗሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ተገንዝበው በወሰዱት ቆራጥ ውሳኔ ያለሙትን ማሳካት መቻላቸውን ድረ ገጹ ለሌሎች አስተማሪነቱን በማመን ለህትመት አብቅቶታል፡፡

የላንዩንግ መንደር የ23 ቤተሰብ አባላት ወይም 80 የሚጠጉ ኗሪዎች አንድ ነጥብ ሁለት የሚረዝም የተሽከርካሪ አውራ ጐዳና ጠርገው ለማጠናቀቅ ዓራት ዓመታት ፈጅቶባቸዋል፡፡

የቾንግኪንግ ክልል ባለስልጣናት መንገዱ በአካባቢው ያለውን ድህነት ለመቀነስ የሚኖረውን ሚና በማረጋገጥ  የቀላል ተሽከርካሪ መንገዱን ማጠናከሪያ እና ለማስፋፋት የወሰኑት በ2016 እ.አ.አ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር  የሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here