ግራንድ ካንዬን ብሔራዊ ፓርክ

0
64

በአሜሪካ አሪዞና ግዛት ሰሜን ምዕራብ ቀጣና ነው  የሚገኘው –  ግራንድ ካንዬን ብሔራዊ ፓርክ፡፡

ፓርኩ ጠቅላላ ስፋቱ አምስት መቶ ሺህ ሄክታር ነው፡፡ ሸለቆው በውስጡ በሚፈሰው የኮሎራዶ ወንዝ  የተበረቦረ ሲሆን ጥልቀቱ 1 ሺህ 500 ሜትር፣ የሸለቆው ስፋት ከ500 ሜትር እስከ 30 ኪሎ ሜትር የተለያየ መሆኑን ድረ ገፆች አስነብበዋል፡፡

ቀጣናው በብሔራዊ ፓርክነት በአዋጅ እውቅና የተሰጠው በ1919 እ.አ.አ በወቅቱ ሀገሪቱን ይመሩ በነበሩት ፕሮዜዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት ነው፡፡

የፓርኩ ከፍታ (የመጨረሻ ጫፍ) ከባህር ወለል በላይ ሰባት ሺህ ጫማ ተለክቷል፡፡ የፓርኩ ቀጣና በደቡባዊ እና ሰሜናዊ ጠርዝ የተከፈለ ነው፡፡

ደቡባዊው ከፍታ ስድስት ሺህ ጫማ በመሆኑ በጉብኚዎች ይዘወተራል፤ ሰሜናዊው ግን አንድ ሺህ  ጫማ ስለሚጨምር ብዙም አይጐበኝምም፡፡

ከደቡባዊው ቀጣና ወደ ሰሜኑ ለመጓጓዝ በተሽከርካሪ 220 ማይል፣ በእግር ለማቋረጥ ግን 21 ማይል ብቻ ነው የሚወስደው፡፡

ፓርኩ ከ90 በላይ አጥቢ የዱር እንስሳት ዝሪያዎች መኖሪያ ነው፡፡ ሀያ ሁለት የሌሊት ወፎች ዝርያዎች መገኘታቸውም ተጠቅሷል፡፡ በአካል ግዙፍ ከሆኑት ኤልክ እና ቢሶን የተሰኙ ወፎች መገኘታቸው ተረጋግጧል ፡፡

በሰሜናዊው ቀጣና ጉድጓድ ቆፍሮ የሚኖረው ቢሶን (ፍልፈል መሰል) እንስሳ ይገኛል፡፡ በተጨማሪ የተራራው አንበሳ፣ አዳኙ (ፑማ) ወይም  “ካውጋር” ወይም “ፓንተር” የተሰኙ   የዱር እንስሳት መኖሪያ ነው፡፡

በተጨማሪም ልዩ ልዩ የእጽዋት ዝርያዎች ይገኙበታል፡፡

ፓርኩ በ1979 እ.አ.አ በዓለም አቀፉ የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት በተፈጥሯዊ ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ናሽናል ፓርክስ ዶት ኦርግ፤ ደብሊው ኤች ሲ፣ ዩኔስኮ ዶት ኦርግ እና ኤንፒ ኤስ ዶት ኦርግን ተጠቅመናል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here