የሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በዞኑ አስተዳደር ሥር ላሉ መምሪያዎች እና ወረዳዎች አገልግሎት የሚውሉ ለተለያዩ መኪናዎች የመኪና የእጅ ዋጋ ጥገና፣ ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ዘይት እና ቅባት፣ ለተለያዩ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል የመኪና ጎማ እና የጊዜያዊ የቢሮ ግንባታ አጥር በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ነጥቦች፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሰሜን ጎጃም ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 08 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ (አገልግሎት) ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት አምስት የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈረም አለበት፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ቢሮው ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ በመውረስ የራሱን አማራጭ ይወስዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር፣ የመኪና ዘይት እና ቅባት ብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር)፣ የመኪና ጎማ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ ብር) እና የጊዜያዊ የቢሮ ግንባታ አጥር ብር ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የመኪና እጅ ዋጋ ጥገና፣ ዘይት እና ቅባት፣ የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን በ4፡30 የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ የጊዜያዊ ቢሮ ግንባታ አጥር በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን 4፡30 የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ በሚከፈትበት ቀን ክብረ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች አማካኘነት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 መቀመጫውን በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 የተባበሩት ማደያ ጀርባ የአማራ ህንፃ ዲዛይን ከተከራየው ቢሮ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የመጫረቻ ሰነዱ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ ዘግይቶ ለቢሮአችን ቢደርስ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑት ድርጅቶች ሁሉንም ዕቃዎች (አገልግሎቶች) በተጠየቀው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በተጨማሪ በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽሎ በቀረበው በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
የሰሜን ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ

