የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/02/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ (ፑል)፣ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጨምሮ ለ2ቱም መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት በመ/ቤቱ የሚገኙ ቀላል ተሽከርካሪዎችን በ2ኛ እና በ3ኛ ደረጃ በግል ጋራዥ በዓመታዊ ኮንትራት ለማስጠገን በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በመ/ቤቱ የሚገኙ ቀላል ተሽከርካሪዎችን በ2ኛ እና በ3ኛ ደረጃ በግል ጋራዥ በአመታዊ ኮንትራት ውል በመያዝ ለማሰራት የሚሣተፋ በባሕር ዳር ከተማ ጋራዥ ቦታ ያላቸው መኖሩን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግዥና /ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 /058 220 96 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ(ፑል)
ባሕር ዳር

