ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
68

በደቡብ ወሎ ዞን የንግስት ዘውዲቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሎት 1. ለሆስፒታሉ ምግብ አገልግሎት ለህሙማን እና ሎት 2. የኮብልስቶን ሥራ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የግንባታ ሥራ ፈቃድ ለኮብልስቶን ሥራ ከደረጃ ቪሲ/ጅ/ጂሲ 7 እና ከዚያ በላይ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ጨረታው ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሆስፒታሉ ምግብ አገልግሎትና የኮብልስቶን ስራ ለ21 ተከታታይ ቀናት ደቡብ ወሎ ዞን በወረኢሉ ከተማ በንግስት ዘውዲቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ዓይነት እና ዝረዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዶች ማግኘት ይችላሉ፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  7. በጨረታ ከሚሰራው ሥራ ጋር በተያያዘ የመልካም ሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ከታወቀ ድርጅት ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. በተሠጠው የጊዜ ገደብ በዲዛይኑ በስራ ዝረዝር  መሰረት አጠናቆ ማስረከብ የሚችል፡፡
  9. በጨረታ አሸናፊው ምክኒያት ስራው ቢጓተት፣ ቢበላሽ ወይም ከዲዛይኑ ውጭ ቢሰራ እና በመሀንዲሱ ከተረጋጋጠ አሸናፊው ድርጅት ኃላፊነቱን  ሙሉ በሙሉ ይወስዳል፡፡
  10. የጨረታ ሰነዶች ከግዥ ፋይናንስ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  11. ማህንዲሱ ባዘጋጀው ሥራ ዝርዝር ውስጥ አንድ ዋጋ ሳይሰጥበት ቢቀር ተጫራቹ (ድርጅት) ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
  12. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋውን (ቫቱን ) ጨምሮ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና  በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሰፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ማንኛውም ተጫራች ተወዳድሮ ባሸነፈበት ዝርዝር ጥቅል ዋጋ መሰረት የውል ማስከበሪያ 30 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ አሽጎ  ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ በንግስት ዘውዲቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በዚያው ቀን 8፡30 ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡
  14. የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ  ከሆነ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በሥራ ቀን እንዲሆን ይራዘማል፡፡
  15. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 14 06 75 89 /09 14 33 01 95 በመደወል ወይም መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የንግስት ዘውዲቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

ወረኢሉ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here