የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
33

በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ሆቴል የሚጣል እቁብ መረዳጃ ማህበር እና በአፈ/ተከሣሽ አቶ ታደለ ታረቀ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈፃፀም ተከሣሽ ንብረት የሆነውን በሽንዲ ከተማ ቀበሌ 01 የሚገኘው በምስራቅ ገነቱ ጌታሁን፣ በምዕራብ ጌጡ ወለላው፣ በሰሜን በልስቲ ዋለ ፣ በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው 202.5 ካሬ ሜትር ቦታ፣ ካርታ ቁጥር 1333መ/ር የሆነውን የአፈፃፀም ተከሣሽ የመኖሪያ ቤት ጥቅምት 10/2019 ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡30 መነሻ ዋጋውን ሣይጠብቅ በ “0” (በዜሮ መነሻ ዋጋ) ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በጨረታ እንዲሸጥ የምዕራብ ጐጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያዘዘ ሲሆን የመኖሪያ ቤቱን በመጫረት መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት  ቤቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እያሣወቅን፤ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ  ያሸነፈበትን ዋጋ ከተቻለ ሙሉውን ካልተቻለ ¼ኛውን ወዲያውኑ የሚያስይዝ መሆኑን እና ቀሪ ገንዘቡን ለጥቅምት 13/2019 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ከረፋዱ በ4፡00 የምዕራብ ጐጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በችሎት ይዞ ቀርቦ የሚከፍል መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

የምዕራብ ጐጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here