ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
55

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ ሎት 1. ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ዞን ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ለምዕራብ ጎጃም ዞን ህብረተሰብ በመንግስት ድጎማ የሚቀርበውን ስኳር በዩኒየኑ በኩል  ለማጓጓዝ ለአንድ አመት በአንድ ዙር 800 ኩ/ል ማጓጓዝ፣ ሎት 2. ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የ2018 ዓ/ም ምርት ዘመን ስንዴ 5000  ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለአጓጓዥ ተጫራቾች የደረቅ ጭነት ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የኦፕሬተር ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብና ማያያዝ የሚችሉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት  የሚችሉ  መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት እና ክብ ማህተም በማድረግ በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት እና ፖስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለስኳር ማጓጓዝ ለ11 ተከታታይ  የሥራ ቀናት  በጋዜጣ የሚቆይ ሲሆን እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እና በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00  ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በእለቱ  በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  5. ለስንዴ ሽያጭ ለ8 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ የሚቆይ ሲሆን እስከ 8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እና በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በእለቱ  በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  7. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየኑ ግዥና ፋይናንስ ዲቪዥን መውስድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማያያዝ አለባቸው፡፡
  9. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  10. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጸ ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም (ሲፒኦ) የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስገባትና ውል መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  11. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚስተናገድ ይሆናል፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 10 32 /640/ 09 00 31 89 07 በመጠየቅ መረዳት ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- የመክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀንና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here