በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ባንክ ደጅ አዝማች ኃይለየሱስ ፍላቴ ቅርንጫፍ እና በአፈ/ተከሣሽ ህብረት ቴክኖሎጅ ኮሌጅ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈፃፀም ተከሣሽ ንብረት የሆኑትን በደምበጫ ከተማ ቀበሌ 01 ውስጥ በአፈ/ከሣሽ ህንፃ ውስጥ የሚገኙት፡- 1ኛ. 108 /አንድ መቶ ስምንት/ የአንድ ሰው መቀመጫ ወንበር፣ 2ኛ. 8 /ስምንት/ ባለ 2 በ60 ሣንቲ ሜትር ጠረጴዛ፣ 3ኛ. 28 /ሃያ ስምንት/ ባለ 1.2 በ60 ሣንቲም ሜትር ጠረጴዛ፣ 4ኛ. 4 /አራት/ ባለ አንድ ተከፋች ቁም ሣጥን፣ 5ኛ. 3 /ሶስት/ የብረት ጠረጴዛ፣ 6ኛ. 2 /ሁለት/ አጭር ሸልፍ፣ 7ኛ. 2 /ሁለት/ ረጅም ሸልፍ፣ 8ኛ. 1 /አንድ/ የስፖንጅ ወንበር፣ 9ኛ. 5 /አምስት/ ትልቅ ቦርድ፣ 10ኛ. 1 /አንድ/ ተሽከርካሪ ወንበር፣ 11ኛ. 5 /አምስት/ የጎማ ወንበር፣ 12ኛ. 16 /አስራ ስድስት/ DELL 755 ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ 13ኛ. 11 /አስራ አንድ/ ዲቫይደር እና 14ኛ. 1 /አንድ/ የማይሰራ ቶሽባ ላፕቶፕ የሆኑትን የአፈፃፀም ተከሣሽ ንብረቶች በ “0” /በዜሮ/ መነሻ ዋጋ ሆኖ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን ንብረቶቹን በመጫረት መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ጨረታው የሚካሄደው ጥቅምት 17/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 መሆኑን እያሣወቅን፤ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ያሸነፈበትን ዋጋ ከተቻለ ሙሉውን ካልተቻለ ¼ ኛውን ወዲያውኑ የሚያስይዝ መሆኑን እና ቀሪ ገንዘቡን ጥቅምት 18/2019 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ በ4፡00 ይዘው ቀርበው የሚከፍሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የምዕራብ ጐጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

