ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
28

የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአልማ በጀት በእንጀኔ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት አንድ ብሎክ ባለ 4 ክፍል የተጀመረውን መማሪያ ክፍል ግንባታ ለማስጨረስ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የተጀመረውን የመማሪያ ክፍል ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወይም ህንፃ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 7 እና በላይ የሆኑ፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የሚገነባውን የግንባታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ከሆነ ለተከታታይ 30 ቀናት የሚቆይ መሆን አለበት ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሚል ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ፣ ስምና አድራሻ በማስቀመጥ ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከነሐሴ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሳጥኑ እስከሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ማስገባት ይጠበቅባችኃል፡፡
  11. የጨረታ ማስታወቂያው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከነሐሴ 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ በሚታሰብ 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ የሚውል ሲሆን በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. በተራ ቁጥር 11 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 773 02 74 /058 773 00 36 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here