በወልድያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በባሕር ዳር ከተማ ፈለገሂወት ሪፈራል ሆስፒታል ህንጻ ጥገና ሥራ የሚውል ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጥገናውን ሥራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ተሳታፊዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፡፡ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) የባንክ ጋራንቲ ዋና /ኦርጅናል/ ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ የተከለከለ በመሆኑ ቢቀርብ ተቀባይነትም የለውም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ 1,500 (አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወልዲያ ከተማ በሚገኘው ገነቴ ኮንስትራክሽን ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ከረፋዱ 4፡30 በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል የሚውልበት ቀን ከሆነ በማግስቱ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጠራና ግልጽ የሆነ የድርጅታቸውን ቴክኒካል ዶክመንት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊም ሳምፕል በማቅረብ የቀረበውም ሳምፕል በአማካሪ መጽደቁ ተረጋግጦ የአቅርቦት ሥራው በራሱ ወጭ ሳይት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛወም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክሰን ጨምሮ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 13 50 49 72 /09 12 91 82 14 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

