በአሜሪካ የካሊፎርኒያ ግዛት ኗሪዋ ጁዲ ኦያማ በ64 ዓመት እድሜአቸው “በስኬት ቦርድ” ውድድር ያስመዘገቡትን ክብረወሰን ከሁለት ዓመታት በኋላም ማስቀጠል መቻላቸውን ዩፒአይ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡
ጁዲ ኦያማ ከ “ስኬት ቦርድ” ወይም በጐማ ተሽከርካሪ ጣውላ ላይ በእግር በመቆም በሰጠ መም ውስጥ በፍጥነት በመወዳደር ለአሸናፈነት መብቃትን በ13 ዓመቷ ወንድሟ በገዛላት መንሸራተቻ መለማመዷ ነው የተገለፀው- በድረ ገጹ፡፡ጁዲ ኦያማ በ1970ዎቹ በአዋቂ ተወዳዳሪነት መሳተፏ እና በ2003 እ.አ.አ “በስላሎም” የዓለም ሻምኘዮና አሸናፊ መሆኗም ተጠቁሟል፡፡
ጁዲ ኦያማ ከልጅነታቸው የጀመሩትን የስኬት ቦርድ ፍቅር ጐልምሰውም ሳይተዉት በ2024 እ.አ.አ በ64 ዓመት ዕድሜያቸው በውድድሩ ሲሳተፉ የዕድሜ ጠገብ ባለክብረወሰንነትን ድል መቀዳጀት አስችሏቸዋል፡፡
አዛውንቷ የሴት ስኬት ቦርድ ውድድር ተሳታፊ ባለክብረወሰንን በ2025 በራሳቸው የተያዘውን ክብረወሰን በ66 ዓመታቸው በመሳተፍ ባለክብረወሰንነታቸውን ማስቀጠል ችለዋል፡፡
ጁዲ ኦያማ ለሚቀጥለው ዓመት በ2027 በሚካሄደው ውድድር ላይ በመሳተፉ 67ተኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ክብረወሰናቸውን በማደስ እንደሚያከብሩትም ነው በማጠቃለያነት የተጠቆመው፡፡
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም


