ማስታወቂያ

0
49

የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ አልኋይ ቀበሌ እና አካባቢው ተወላጆች የሆኑት 19 አባላት ያሉት የበጎ አድራጎት ልማት ማህበር ለመመስረት እና ህጋዊ እውቅና ለማግኘት የበጎ አድራጎት እውቅና ድርጅቶችና ማህበራት መመዝገቢያ እና መተዳደሪያ አዋጅ ቁጥር 194/2004 በሚፈቅደው አግባብ ህጋዊ እውቅና እንዲያገኝ ጠይቋል፡፡ ስለሆነም የበጎ አድራጎት ልማት ማህበሩ ስያሜ እና አርማ (ሎጎ) መመዝገብ የሚቃወም ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት መቃወሚያዉን ይዘው አማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የሰሜን ጐጃም ዞን ፍትህ መምሪያ የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የሰነዶች፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ማህበራትና የጠበቆች ምዝገባ ይዘው እንዲቀርቡ እያሣወቅን እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ ካልቀረቡ የቀረበውን ስያሜ እና አርማ (ሎጎ) የምንመዘግብ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here