ግዮን የማህበረሰብ አቅም ግንባታ ለዘላቂ ልማት የበጎ አድራጎት ማህበር እንዲመዘገብ እና ድርጅቱ (ማህበሩ) የሚጠቀምበት ከታች የተቀመጠው አርማ (ሎጎ) ህጋዊ እውቅና እንዲሰጣቸው በ21/12/18 ዓ/ም በተፃፈ ማመልከቻ ጠይቋል፡፡ ስለሆነም የድርጅቱን ስያሜ እና አርማ (ሎጎ) መመዝገብ የሚቃወም ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት መቃወሚያዉን ይዘው አማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የሰነዶች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የጠበቆች ጉዳይ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 እንዲቀርቡ እያሣወቅን እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ ካልቀረቡ የቀረበውን ስያሜ እና አርማ(ሎጎ)የምንመዘግብ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡
አማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ

