ታዳጊዎችን ከድካም ያላቀቀው

0
55

በቻይና ዩናን ግዛት ከተራራ ስር ባለ መንደር የሚገኙ ታዳጊዎች በተራራው አናት ወደሚገኝ ትምህርት ቤት ለመድረስ ይወስድባቸው የነበረውን የሦስት ሰዓታት ጉዞ ወደ  30 ደቂቃ የሚያሳጥር ውጪያዊ አሳንሰር መገንባቱን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

በ2022 እ.አ.አ 268 ሜትር የሚረዝም ኩዊንግዩን የተሰኘ አሳንሰር ተገንብቶላቸው እንደነበር ያስነበበው ድረ ገጹ ከታዳጊዎቹ ብዛት አንፃር  ተሰልፈው ስለሚቆዩ ሦስት ሰዓታት ጊዜ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ይህንን የተመለከቱት የግዛቱ አስተዳደር አካላት ለችግሩ  መፍትሄ ይሆን ዘንድ በተጨማሪነት የ“ፉያ ኦ” አሳንሰርን ለመገንባት መገደዳቸው ነው የተገለፀው፡፡

ከነባሩ የኩዊንግዩን አሳንሰር ጐን የተገነባው የፉያኦ አሳንሰር ከነባሩ 20 ሜትር ጨምሮ ርዝመቱ 288 ሜትር፣ ስፋቱም ሆነ ፍጥነቱ የተሻለ እንደሆነ ድረ ገጹ አስፍሯል፡፡

በተጨማሪነት የተተከለው የፉያኦ አሳንሰር ሦስት ሰዓታት ይወስድ የነበረውን የጊዜ ምጣኔ ወደ ሰላሳ ደቂቃ ማሳጠር ችሏል፡፡ በዚህም የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቦ መነጋገሪያ ርእሰ ሊሆን መቻሉን ነው በማጠቃለያነት ድረ ገጹ ያስነበበው፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመስከረም 4  ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here