መንጃ ፈቃድ ሳይኖረው ያሽከረከረው ዓይነስውር

0
35

የ50 ዓመቱ እንግሊዝያዊ አይነስውር መንጃ ፈቃድ ሳይኖረው ፣በምሽት ጠጥቶ 241 ኪሎ ሜትር አሽከርክሮ አደጋ ሳያደርስ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ቢውልም በፍርድ ቤት ጥፋተኛነቱ በመረጋገጡ በእስራት፣ በእንቅስቃሴ ገደብ እና ማገገሚያ ውስጥ እንዲቆይ የተወሰነበት መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

በእንግሊዝ ሀርድ ፊልድ በተሰኘ ቀጣና ኗሪው ሰኔ 29 ቀን 2026 እ.አ.አ “ኤም 6” በተሰኘ አውራ ጐዳና በኦፔል ሜሪቫ መኪና ከመስመር መስመር እየተጠማዘዘ በዘፈቀደ ሲያሽከረክር በፓሊስ መኮንኖች እይታ ውስጥ ሊገባ ችሏል፡፡ አሽከርካሪውን አስቁመው ሲጠጉትም አንቶኒ ሆል አልኮል መጠጣቱንም ሆነ መንጃ ፈቃድ የሌለው መሆኑን አምኗል፡፡

አሽከርካሪው ከባለቤቱ ጋር ባጋጠመው ጠብ እና የገንዘብ ችግር ተበሳጭቶ የባለቤቱን ተሽከርካሪ አስነስቶ ወደ ስኮትላንድ በሚወስደው አውራ ጐዳና ማምረቱን አስረድቲል፡፡ ኦንቶኒ ሆል ነዳጅ አልቆበት ለመቅዳት በቆመበት ማደያ ስፍራ የነበሩ ሰራተኞች ዓይነስውርነቱንም ሆነ አልኮል መጠጣቱን አለመገንዘባቸውን ከፓሊስ  ለቀሩበላቸው ጥያቄ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም  አልኮል ጠጥቶ የሰከረ ዓይነስውር ሰው መንጃ ፈቃድ ሳይኖረው እንዴት 241 ኪሎ ሜትር ማሽከርከር ቻለ? ለሚለው የፓሊስ ጥያቄ አንቶኒሆል ሙሉ በሙሉ የማየት ችሎታውን ካጣ ሁለት  ዓመቱ መሆኑን እና በሚሄድበት አቅጣጫ ይጓዝ ከነበረ ከባድ የጭነት መኪና ኋላ በመከተል የኋላ መብራት ወጋገንን እና ድምጹን ተከትሎ መጓዙን አበራርቷል፡ ያም ሆኖ ፍርድ ቤቱ የዘጠኝ ወር እስራት፣ የ18 ወራት የእንቅስቃሴ ገድብ እና ለሦስት ወራት ማገገሚያ ውስጥ እንዲቆይ ተወስኖበታል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመስከረም  18 ቀን 2019  ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here