የአካባቢ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
32

የአዲስ ዘመን ፋና አካታች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ከአልማ ጋር በመተባበር  በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክት ለሚተገበረው የዶሮ እርባታ ሥራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በአካባቢ ግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚገዙ ዕቃዎች፡-

1 የዕቃው ስም መጠን/ዝርዝር ብዛት
2 የ45 ቀን እንቁላል ጣይ ዶሮ ቦቫንስ ብራውን፣ ጤናማና የክትባት ማረጋገጫ ያለው 21,075 ዶሮ
3 የዶሮ መኖ 45 ቀን ዕድሜ ላላቸው ዶሮዎች የሚሆን Grower/Developer 220 ኩንታል
4 የዶሮ መጠጫ 6 ሊትር የመያዝ አቅም ያለው 440 ቁጥር
5 የዶሮ መመገቢያ 6 ኪ.ግ መኖ መያዝ አቅም ያለው 440 ቁጥር
6 ፎርማሊን የዶሮ ቤት ማጽዳት /መከላከያ 110 ሊትር
7 Virkon ፀረ-ተህዋሲያን 110 ሊትር

 

የተጫራቾች መስፈርት፡-

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ቲን ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. አስፈላጊውን የግብር ቫት ማስረጃ የሚያቀርቡ፣ በጨረታ ሰነዱ የተጠየቁትን ሌሎች ማስረጃዎች የሚያቀርቡ፡፡
  3. የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ ክፍያ በመክፈል ከፋና አካታች ቢሮ፣ አዲስ ዘመን ከተማ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋቸው አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) በሲፒኦ ወይም Unconditional Bank Guarantee ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይቆያል፡፡
  6. የመጨረሻ ማቅረቢያ በ10ኛው የሥራ ቀን 9፡00 ይሆናል፡፡
  7. የጨረታ መክፈቻ ቀን በዚያው ቀን 10፡00 የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን 3፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊው ከተለየ በኋላ 50 ቀን የማቅረቢያ ጊዜ ይሰጠዋል፡፡
  9. የመክፈቻ ቦታ፡ ፋና አካታች ቢሮ፣ አዲስ ዘመን ከተማ ነው፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ቦታ አዲስ ዘመን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጀ ፋና አካታች ህብረት ሥራ ማህበር፣ ጽ/ቤት (ቢሮ) ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 65 85 72 45 /09 92 38 70 82 /09 18 45 44 69 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የእያንዳንዱ ዕቃ ዝርዝር ቴክኒካዊ መስፈርት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡

የአዲስ ዘመን ፋና አካታች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here