በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በክልሉና በከተማዉ በጀት ድጋፍ በከተማዉ ውስጥ የቢሮ የህንፃ ግንባታ G+3 ቀሪ ስራዎች ለማስጨረስ ፓኬጅ ቁጥር AM DEJEN/CP/CW/07/2020/2021 lot2 የጉልበት የእቃና የማሽነሪ ግዥዎችን ጨምሮ መስፈርቱን የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግንባታ ግዥው ወይም ዋጋው ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- GC/ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ እና BC ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ወደ ፋይናንሽያል ለማለፍ ቢያንስ 70 በመቶ የቴክኒካል ዶክመንት ውጤት ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የስራዉ ዝርዝር መግለጫ ከተዘጋጀው /SBD/ የተጫራቾች መመሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የግንባታ ተጫራቾች እያንድንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,200 (አንድ ሽህ ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከደጀን ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ25 ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1,600,000 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በግዥ መመሪያዉ መሰረት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ የቴክኒካልና ፍይናንሻል ዶክሜንት በጥንቃቄ በታሸገ የተለያየ ፖስታ በፖስታው ላይ አድራሻውን በመፃፍ ደጀን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 26ኛዉ ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ 3፡50 ይታሽጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 18 በ26ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 18 ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 00 24 /058 776 10 09 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደጀን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

