ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ  ጊዜ የወጣ  ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
37

በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1. አሮጌ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሎት 2. ሰብል ሸያጭ ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸዉ ፍቃድ የተሰጣቸዉ(በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥዉ የሚሳተፍ ማንኛዉም ተጫራች ተጨማሪ እስት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት፡፡እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና ሲፒኦ ሲያሲይዙ ቫት የሚጠይቁትን ጨምሮ መሙላትና ማስያዝ አለባቸሁ፡፡ የሚጠይቀዉ የአንድ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚውጣውን እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጣ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ዉስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ  የሰራ  ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ጨርታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሰራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00  ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለሁለተኛ  ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ  ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ቅዳሜ ለዩኒየኑ የስራ ቀን ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው ተወዳዳሪዎች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከሎት ውስጥ ግን የንግድ ፍቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፡፡
  12. በሎት 1 ላይ የተጠቀሱት አሮጌ ያገለገሉ ዕቃዎች ውስጥ ከሎት 1.ሀ እሰከ ሎት 1 ሐ ድረስ በሶስት ደረጃ የተመደበ ሰለሆነ ከሎት 1ሀ እሰከ ሎት 1ሐ ድረስ የፈልጉትን መርጦ መሙላት ይቻላል፡፡
  13. አሸናፊው ያሸነፈዉን እቃ በእሱ ትራንስፖርት አጓጓዞ ሊወስድ ነዉ፡፡ የሚሸጡ ማንኛዉም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛሉ፡፡ አሽናፊው የሚለየው በተናጠል ነው፡፡
  14. አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ዕቃ ሽያጭ በፍትህ ዉሉ ከተመረመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊዉ ይከፍላል፡፡ ሰብሉን ለማንሳት የሚያሰፈለጉ ማንኛውም የወዛደር ማሰጫኛ እና የትራንሰፓርት ወጭዎች አሽናፊው የሚሽፍን ይሆናል፡፡ ሎት2 ሰብል ሽያጭ የሚለው የተለያየ ሰብል ሰለሆነ የሚፈልጉትን ሰብል  ሁሉንም ወይም ለይቶ መሞላት ይቻላል፡፡
  15. ሰብሉ የሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዘን የሚገኝ ሲሆን የሩዝ ሰብል ሽያጭ የሚገኝበት  ቦታ ሃሙሲት መጋዝን ሲሆን፤ አሸናፊው መጋዝን ላይ ያለውን ሰብል ለማንሳት ፈቃደኛ የሆነ እና ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት ይቻላል፡፡
  16. በዚህ ያልተጠቀሱ ሃሳቦች ቢኖሩ በህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
  17. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 11 59 05 34/ 05 83 20 16 70 መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here