በምስራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሳሪያ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ይመለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ግዥው ወይም ዋጋው ከብር 500‚000 (ከአምስት መቶ ሽህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥው ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከደጀን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ10 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ እና በጨረታው ላይ ችግር ቢከሰትና ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ በራሳቸው ምክንያት ውል ባይፈጽሙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ መሆኑንና ካሸነፉ ለውል ማስከበሪያ 10በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በግዥ መመሪያዉ መሰረት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሁሉንም መስፈርቶች በፖስታው ላይ በማሟላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የሚመለከታቸውን ሰነዶች በሙሉ በማድረግ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በጀርባው ላይ የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ደጀን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን 3፡50 ይታሸጋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነና ለመለየት አሻሚ ከሆነ ዋጋ አይኖረውም፡፡
- መ/ቤቱ ከሚገዛው እቃ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 18 በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚለዩት ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ይሆናል፡፡
- የመክፈቻ ቀኑ በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር18 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 00 24 /058 776 10 09 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደጀን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

