ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
24

የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ሰ/ምዕ/ሪጅን/ትራ/ሰብ/ኦፕ ጥገና ቢሮ  በሪጅኑ ስር በሚገኙ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ እና ትራንስሚሽን መስመር ጥገና የሰርቪስ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ሚኒባስ እና አይሱዚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ   መግዛት ይፈልጋል፤ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትን  ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ዋስትና ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንት) ከ90 ቀን በታች የሆነ ባንክ ጋራንት ተቀባይነት የለውም ፤ ማስያዝ ግን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በኢ.ኤ.ኃይል ሰ/ምዕ/ሪጅን ትራ/ሳ/ኦፕ ሂሳብ ቁጥር 1000142876087 ገቢ በማድረግ ዝርዝር ጉዳዩን የያዘ ሰነድ በኢ.ኤ.ኃይል ሰ/ምዕ/ሪጅን ትራ/ሰብ/ኦፕ ከፖሊ ወደ ጋንቢ በሚወስደው መንገድ ከፍትህ ቢሮ አለፍ  ብሎ በሚገኘው ህንፃ 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልጽ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም የተወዳደሩበትን ከፖስታው ላይ በትክክል በመግለጽ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድነት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ  ከወጣበት ከጥቅምት 02/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ  ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት  ለዚሁ ጨረታ ለማገልገል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ  ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ኢትዬጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ይከፈታል፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  7. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 226 6509/058 222 0829 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች ከመስሪያ ቤቱ ጋር ማሸነፉ በተገለጸለት በ5 ቀን ውስጥ ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ሰ/ምዕ/ሪጅን/ትራ/ሰብ/ኦፕ ጥገና ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here