ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
35

በአማራ ቤቶች ልማት ድርጅት የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሰራተኞች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የደንብ ልብሶችን ማለትም ሸሚዝ፣ 6ሺ-ቲትረን ልብስ፣ ጫማ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ስፌትን ጨምሮ እንዲሁም የግንባታ ግብዓቶችን በቀረበዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸዉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአማራ ቤቶች ልማት ድርጅት ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቀበሌ 04 ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው የጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 103 በመምጣት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈልና የጨረታዉን ሰነድ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛዉ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው እና ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ገቢ ግብር ለመክፈሉ ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣቱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. አሸናፊው ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና (ፐርፎርማንስ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለበት፡፡
  7. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ማለትም ጥቅምት 23/2019 ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 106 ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት የደንብ ልብሶችን እና ሌሎችንም በራሱ ሙሉ ወጭ በቤቶች ልማት ድርጅት ባሕር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 220 11 87 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአማራ ቤቶች ልማት ድርጅት ባሕር ዳር ቅ/ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here